ከተማችን ምቹ በማድረግ ወጣቶችን እና የስፖርት...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ከተማችን ምቹ በማድረግ ወጣቶችን እና የስፖርት ቤተሰቡን ማዕከል ተደርገው የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ ናቸው/ አቶ በላይ ደጀን/

ከተማችን ምቹ በማድረግ ወጣቶችን እና የስፖርት ቤተሰቡን ማዕከል ተደርገው የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ ናቸው/ አቶ በላይ ደጀን/ ሕዳር 1 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ከተማችን ምቹ በማድረግ ወጣቶችን እና የስፖርት ቤተሰቡን ማዕከል ተደርገው የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ ከመሆናቸው ባሻገር ነገ አስተሳስሮ ዘመኑን የሚዋጅ ተግባራት ናቸው ሲሉ ገለጹ፡፡ በመደመር መንግስት መጽሐፍ በወጣቶች እየተካሄደ የሚገኘው የፓናል ውይይት መንግስታችን እየሰራ ያለውን ስራ ወጣቱ እንዲገነዘብ ያስችላል ያሉት አቶ በላይ ስራዎች ከዕቅድ አልፈው መሬት ላይ ወርደው እልፍ ተጨባጭ ውጤት መመዝገባቸውን የሚያሳዩ የጉብኝት ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡ አገልግሎታችን በማዘመን ውጤታማነታችን ለማረጋገጥ በስፖርት ማዘውተርያ ስፍራዎች እና በወጣት ሰብእና ማዕከላት ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እንደሚሰራ የገለጹት አቶ በላይ የተቋሙ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሻጋሪ ስራ ለመስራት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው አመላክቷል፡፡ በ2ኛው ኦሎምፒክ ጨዋታ በብቃት ከማዘጋጀት ባለፈ የተገኘው ውጤት ጨምሮ በስራ ዕድል ፈጠራ የተሠጠው ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ አበረታች ነው ያሉት አቶ በላይ ሰፓርትን የቱሪዝም አካል ለማድረግ እና ስፓርታዊ ባህሎቻችን ለማዳበር የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.