የትምህርት ቤቶች ውድድርን አስመልክቶ ዛሬ ከሰዓ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የትምህርት ቤቶች ውድድርን አስመልክቶ ዛሬ ከሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል

ፕሬስ ሪሊዝ

ግንቦት 6 2016 ዓ/ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተናጋጅነት የሚካሄደውን የሁለተኛ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ስፓርታዊ ውድድርን አስመልክቶ ዛሬ በትምህርት ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ተገለጸ

በስድስት የስፓርት ዓይነቶች የሁሉም ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚሳተፉበት ውድድሩ በከተማው ውስጥ ያሉትን ተማሪዎች በማቀራረብ ተጠናከረ የወዳጅነት መንፈስ እንዲኖር የሚያስችል ሰፊ የስፖርት ንቅናቄ መሆኑ ተገልጽዋል

በ11ዱም ክፍለ ከተማ ያሉ የመንግስት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርት ቤታቸውን ወክለው በአትሌቲክስ በእግር ኳስ በቮሊቦል በእጅ ኳስ በቅርጫት በጠረጴዛ ቴኒስ በሁለቱም ጾታ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል

ስፓርታዎ ውድድሩ በ11ዱም ክፍለ ከተማ በክላስተር ዉድድር ተደርጎ አሸናፊ የሆኑ ት/ቤቶች በቀጥታ ራሳቸዉን ችለዉ እንደሚሳተፉ የውድድር ስርዓቱ መረጃ የሚያስረዳ ሲሆን በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚካሄደውን ውድድር ስፖርት ጽ/ቤት እና ትምህርት ጽ/ቤት እንደሚመሩት ተገልጽዋል

ተተኪና ሀገር ተረካቢ የሆነዉን ትዉልድ በተለያዩ የስፖርት እንቅስቃሴዎች በማሳተፍ በአካልና በአእምሮ የዳበሩ በማድረግ ሀገራችን ከያዘቸዉ የእድገትና ብልጽግና ጉዞ ዉስጥ አንዱ ስፖርት መሆኑ ተመላልክቷል

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና የመምህራን ስፓርታዊ ውድድር ከግንቦት 10 እስከ 24 2016 ዓ/ም የሚካሄው ይሆናል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.