ቢሮው የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ድጋፍና ክትትል ግኝቶች ላይ ውይይት አካሄደ ሕዳር 2 ቀን 2018
ቢሮው የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ድጋፍና ክትትል ግኝቶች ላይ ውይይት አካሄደ ሕዳር 2 ቀን 2018 ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት 1ኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል ሪፓርት ላይ ከማዕከላት ስራ አስኪያጆች እና ከክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀመጠ ቢሮው በባለቤትነት የሚያስተዳድራቸው የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ለወጣቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር-ዓለም ደምሴ የወጣቶች ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል የወጣት ማዕከላት ለትውልድ ግንባታ በሚል መሪ ሃሳብ ከተማ አቀፍ ንቅናቄ እንደሚደረግ ያስታወቁት አቶ ክብር-ዓለም ሃብት በማፈላለግ ሞዴል ማዕከል በማድረግ ለሚስሩ ውጤታማ ሥራ አስኪያጆች ዕውቅና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል ወጣቶችን እያለማን ስብዕናቸውን እየገነባን በአካል በስነ ልቦና በማነጽ ስኬቶቻችን ማስተዋወቅ ስራ ላይ በትኩረት መስራት አለብን ያሉት የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ንብረት ይሁኔ ማዕከላት የተሰጣቸውን ተልእኮ በብቃት ለፈጸም እየተካሄደ የሚገኘው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል በድጋፍና ክትትሉ ከ114 የወጣት ስብዕና ማዕከላትን 40ው ማካተቱን የገለጹት የወጣት ስብዕና መገንቢያ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሳሙኤል ምትኩ ያላቸውን ጥንካሬ ክፍተቶች ከነ መፍትሄ አቅጣጫዎች በዝርዝር አቅርበዋል ማዕከላቱ በወጣቱ በሚፈልገው ደረጃ ሳቢና ማራኪ ለማድረግ ስራ አስኪያጆች ባላቸው አቅም መስራት እንዲለባቸው ያመላከቱት አቶ ሳሙኤል ወቅቱን የጠበቀ የኦዲት ስራ ማካሄድ፣ ከትልቅ ገብነት ነጻ ማድረግ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል በድጋፍና ክትትሉ የተገኙ ግኝቶች ላይ በመድረኩ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመፍታት ሁሉንም ተቋማት ሞዴል ለማድረግ ባሉ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ማዕከላትን በግብአት ማደራጀት ለነገ የማይባል ተግባር ነው ያሉት በሪፓርት ግምገማው የተሳተፉ የማዕከላት ሥራ አስኪያጆች እና ቡድን መሪዎቹ ቢሮው የወጣት ስብእና መገንቢያ ማዕከላትን በባለሙያ በአደረጃጀት እና በአሰራር ለማዘመን እየስራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ አቶ ክብር-ዓለም በሰጡት የስራ አቅጣጫ የማዕከላቱን ጣልቃ ገብነት ችግርን ለመፍታት አመራሩ በትኩረትና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አመላክተው ድጋፍና ክትትሉ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከመዳሰስ ባለፈ እቅድን አፈጻጸምን የመከታተል ስራ እንደሚጠናከር አመልክተዋል ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014 ትዊተር https://twitter.com/compose/tweet ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/ ኢንስታግራም https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/ ኢሜል addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.