የመደመር መንግስት የወጣቶች የፓናል ውይይት በመ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የመደመር መንግስት የወጣቶች የፓናል ውይይት በመደመር ትውልድ የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራ ላይ ተካሄደ

የመደመር መንግስት የወጣቶች የፓናል ውይይት በመደመር ትውልድ የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራ ላይ ተካሄደ

ሕዳር 4 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አህመድ የተጻፈውን አየመደመር መንግስት መጽሐፍ የወጣቶች የፖናል ውይይት በመደመር ትውልድ የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራ አካሄደ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተጻፈው የመደመር መንግስት አራተኛ መጽሐፍ ዙሪያ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ጋር ዛሬ ውይይት ተካሂዷል

ሥነ ጽሑፍ አገርን የመለወጥ ትልቅ አቅም እንዳለው በመረዳት ጸሐፍት በርካታ ሙከራዎች ቢያደርጉም እንዳልተሳካላቸው የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር ዓለም ደምሴ በጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አህመድ የተጻፉ አራቱ መጻሕፍት በአጭር ጊዜ መሰረታዊ ለውጥ ያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኮዲንግ እና የዲጂታል ክህሎት ስልጠናዎችን ወጣቶች በማሰልጠን መቻሉ የመደመር መንግስት መገለጫ ነው ያሉት አቶ ክብር-ዓለም ትውልደዱ በቴክኖሎጂ መሰረታዊ እውቀትን በማግኘት ዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን መቻሉን አውስተዋል፡፡

የመደመር መንግስት መጽሐፍ ፖለቲካ፣ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚና የማህበረሰባዊ ክንውኖችን በጥልቀት የሚዳስስ መሆኑን ያወሱት አቶ ክብር -ዓለም መጽሐፉ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት እንድንላቀቅ በርካታ አመላካቾች እንዳሉት አስገንዝበዋል

መደመር የስፓርት ማዘውተርያ ስፍራ በጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አሕመድ የመጀመሪያ መጽሐፍ ሽያጭ መገንባቱን ያስታወሱት የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፓርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል አበበ የመደመር መንግስት የወጣቶችን ሁለንታዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል

የመደመር መንግስት መጽሐፍ መዳረሻውን ብልጽግና ያደረገ አሻጋሪ ሃሳቦችን ይዟል ያሉት አቶ ሳሙኤል የብልጽግና ተስፋዎችን እውን ለማድረግ ወጣቶች የተጣለባቸውን ትልቅ ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመጽሐፉ ዙሪያ እየተካሄደ የሚገኘው የወጣቶች የፓናል ውይይት ነገ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እንደሚካሄድ የወጣቶች ግንዛቤ እና ንቅናቄ ዳይሬክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.