የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር በትምህርት ቤት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር በትምህርት ቤት ደረጃ ተጀመረ። ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም

የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር በትምህርት ቤት ደረጃ ተጀመረ። ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት የ2018ዓ.ም የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር በትምህርት ቤት ደረጃ ተጀመረ። በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ትምህርት ቤቶች የተተኪ ስፖርተኞች መፍለቂያ ተቋማት ናቸው ብለዋል። የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት የስልጠና ፕሮጀክቶችን በትምህርት ቤቶችም እንዲስፋፋ እየተደረገ መሆኑንን የተናገሩት አቶ ዳዊት በትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ከውድድር ባለፈ በተማሪዎች መካከል የእርስ በእርስ ግንኙነትን የሚያጠናክር ነው ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ አሊ ከማል በትምህርት ቤት ደረጃ የሚካሄድ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር በአካል እና አዕምሮ የዳበረ ዜጋ ለመፍጠር ይረዳል ብለዋል። ውድድሩ በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ተጀምሮ ንዲጠናቀቅ ተማሪዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አቶ አሊ ጥሪ አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳ ፣ በክፍለ ከተማ እና በከተማ ደረጃ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው ውድድሩ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቢሮው በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቀዋል። በስነ ምግባር የታነፀ እና ጤናው የተጠበቀ ትውልድ ለማፍራት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ጠቃሚ መሆኑን አቶ ዲናኦል ጠቅሰዋል፡፡

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.