የተገልጋይ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ህዳር 05 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የተገልጋይ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ህዳር 05 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የተገልጋይ ቀንን ምክንያት በማድረግ የአንድ ማዕከልን አገልግሎትን ጨምሮ ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
የቢሮው ሀላፊ የሆኑትን አቶ በላይ ደጀንን ጨምሮ ሌሎች የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች አገልግሎት ፈልገው ለመጡ አካላት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል።
ተገልጋዮች ቢሮው ዘወትር እሮብ እና አርብ ለተገልጋይ ቅድሚያ በመስጠት እየሰራው ያለው ስራ መልካም መሆኑን ገልፀው ባገኙት ቀልጣፋ አገልግሎት መደሰታቸው ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ዘወትር እሮብ እና አርብ ከሌሎች ቀናት በተለየ መልኩ ለተገልጋዮች ከጠዋቱ 2:00 እስከ ምሸቱ 11:30 አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል።
Comments
ምንም አልተገኘም.




አስተያየቶችዎን ይተዉት.