ቢሮው በ20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች...

image description
- ውስጥ supporter    0

ቢሮው በ20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አከባበር ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

ቢሮው በ20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አከባበር ዙሪያ ውይይት አካሄደ። ህዳር 05 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች አከባበር ዙሪያ ከክፍለ እስከ ወረዳ ካሉ የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያች ጋር ውይይት አካሂዷል። በዓሉ ''ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ማዕቀፍ የተገነባ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር የሚያደርጉ የተለያዩ ስራዎች እነሰደሚሰሩ በውይይቱ ተነስቷል። የከተማው ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች የሚሳተፋበት እና ህብረ ብሔራዊ አኔድነትን የሚያሳዩ የፖናል ውይይች፣ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች፣ የብስክሌት ጉዞዎች እና የተለያዩ ስፖርታዊ ሁነቶች እንደሚዘጋጁ በውይይቱ ተመላክቷል። በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራን የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን የህዳሴ ግድባችንን አጠናቀን ባስመረቅንበት በወቅት የሚከበር በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። በዓሉን በተለያዩ ሁነቶች ማክበር ስለ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ግንዛቤን በመፍጠር አንድነትን ለማጠናክር ያግዛል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ወጠቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አካላት አዲስ አበባ ህብረ ብሔራዊት ከተማ መሆኗን የሚያሳዩ ሁነቶችን እና የግንዛቤ ማስጨበጫ የፖናል ውይይቶችን እንደሚያዘጋጁ ተናግረዋል። ከህዳር 6 እስከ 19 /2018ዓ.ም 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በከተማ ደረጃ በተለያዩ ሁነቶች እንደሚከበር ተመላክቷል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.