ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የወጣቶች እ...

image description
- ውስጥ supporter    0

ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ሚና የጎላ ነው። አቶ በላይ ደጀን

ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ሚና የጎላ ነው። አቶ በላይ ደጀን ህዳር 08 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ 20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ሁነቶች እያከበረ ይገኛል። ''ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ቃል ከብሎክ አደረጃጀቶች ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ የወጣቶች የፖናል ውይይቶችን እና ስፖርታዊ ሁነቶችን በዓሉን ምክንያት በማድረግ እየተካሄዱ መሆኑን አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ተናግረዋል። ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰብች ሚና የጎላ መሆኑን የገለፁት አቶ በላይ ደጀን በሐሳብ የበላይነት እና በውይይት የሚያምን ወጣት ለሀገር ሁለንተናዊ አድገት ወሳኝ ነው ብለዋል። ወጣቶች በሀገራቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው የገለፁት አቶ በላይ ህብረ ብሔራዊነቶ የተረጋገጠ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንደሀገር እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ በመሳተፍ አሻራቸውን እንዲያስቀምጡ አሳስበዋል። 20ኛው የብሐር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን እኛ ኢትዮጵያዊያያን ህዳሴ ግድብን አጠናቀን ባስመረቀንበት አመት የምናከብረው በመሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል። በቀጣይ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ የወጣቶች የፖናል ውይይት እና የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃስ መርሀ ግብር እንደሚካሄድ አቶ በላይ አሳውቀዋል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.