ባለፋት 4 ወራት ከ193ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ባለፋት 4 ወራት ከ193ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል። ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ህዳር 09 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለፉት 4 ወራት ለከተማው ወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር እና ወጣቶች ክንፍ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ቢሮው ባፉት 4 ወራት ከ193ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች በስራ እድል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል። ስራ አጥ ወጣቶችን ከመመዝገብ ጀምሮ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የማይድ ሴት ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ፣ በከተማው ያሉ የስራ እድል ፀጋዎች በመለየት የተግባር ስልጠና መስጠት፣ ከአሰሪ ድርጅቶችና ባለሀብቶች ጋር ወጣቶችን የማገናኝት ስራ በቀጣይ ትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ አቶ በላይ አሳስበዋል። ወጣቶች ስራ የማማረጥ ዝንባሌ መኖር፣ በቅንጅት እና በትስስር ከመስራት አኳያ ክፍተት መኖሩ እና ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን በብዛት እንዲፈሩ አለማድረግ ባለፋት 4 ወራት ቢሮው በስራ ድል ፈጠራ ላይ ያጋጠሙት ተግዳሮቶች እንደነበሩ ተመላክቷል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.