15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ቅዳሜ ሕዳር 13 ይጀምራል።

15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ቅዳሜ ሕዳር 13 ይጀምራል። ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አዘጋጅነት የሚካሄደው 15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር ቅዳሜ ሕዳር 13 ይጀምራል። ውድድሩን እና ፌስቲቫሉን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ በአስተናጋጁ በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ተሰጥቷል። ''አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት'' በሚል መሪ ቃል ከሕዳር 13 እስከ ሕዳር 24/2018ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ውድድር እና ፌስቲቫል ሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚሳተፋ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ተናግረዋል። በ7 የስፖርት አይነት ከ12ሺህ በላይ አካል ጉዳተኛ እና መስማት የተሳናቸው ስፖርተኞች እንደሚሳተፋ የገለፁት አቶ ዳዊት በውድድሩ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ስፖርተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ወክለው እንደሚሳተፉ ተናግረዋል። በየአመቱ የሚካሄዱ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድርና ፌስቲቫል በከተማችን ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች እውቅና ከመስጠቱ ባሻገር ማህበራዊ እና ኢከኖሚያዊ ተሳታፊነታቸውን እና ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያረጋግጥ አቶ ዳዊት በመግለጫቸው ላይ ገልፀዋል። ሴቶችና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ማህበራዊ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው በኩላቸው ስፖርታዊ ውድድሩና ፌስቲቫሉ የአካል ጉዳተኞችን የስፖርት ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። የአካል ጉደተኞች ቀን በአገራችን ለ33 በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ እየተከበረ ወ/ሮ ገነት ተናግረዋል። የካ ክፍለ ከተማ ውድድሩን ለማዘጋጀት በቂ ዝግጅት ማድረጉን የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የስራ እና ክህልት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት ተናግረዋል። 15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድርና ፌስቲቫል ቅዳሜ የካ ክፍለ ከተማ በሚገኝው 28 ሜዳ በድምቀት እንደሚጀመር ተመላክቷል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.