በማዕከላት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በማዕከላት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከውጤታማ ሥራ አስኪያጆች ልምድ ሊወሰድ ይገባል/አቶ በላይ ደጀን/ ሕዳር 12 ቀን 2018 ዓ/ም

በማዕከላት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከውጤታማ ሥራ አስኪያጆች ልምድ ሊወሰድ ይገባል/አቶ በላይ ደጀን/ ሕዳር 12 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከውጤታማ ሥራ አስኪያጆች እና ማዕከላት ልምድ ሊወስድ እንደሚገባ አሳሰቡ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ሥራ አስኪያጆች የክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች በልማትና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ከቢሮ ኃላፊው ጋር በአራት ኪሎ ስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ተወያይተዋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የወጣቶች ፍላጎት ለማርካት የመደመር ሕሳቤ የሆነውን መፍጠር፣መፍጠን እና መዝለልን ተግብራዊ ማድረግ እንደሚገባ አቶ በላይ አሳስበዋል በየማዕከላቱ የተለዩ ችግሮች በመፍታት አገልግሎት አሰጣጡ ለወጣቱ የሚመጥን እንዲሆን በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ በላይ ሥራ አስኪያጆች የወጣቶችን አቅም በመጠቀም የአመራር ጥበብ በመላበስ ከፊት ሆኖ የመምራት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል በራስ አቅም ማዕከላትን ማስዋብ እና ማራኪ ማድረግ የሥራ አስኪያጆች ትንሹ ተግባር ቢሆንም ክፍተቶች እንዳሉ የጠቀሱት አቶ በላይ የመብራት፣ የውሃ እና የዕድሳት ጥያቄን በላው መዋቅር ለመፍታት ሥራ አስኪጆች ፕሮፖዛል በመንደፍ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በየማዕከላቱ በተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ገለጻ ያደረጉት የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ቡድን መሪ አቶ ሳሙኤል ምትኩ የወጣት ማዕከላት የጣልቃ ገብነት፣ ከኤሌክትሪክ ኃይል ጋር የተያያዘ እና ይዞታ አለመረጋገጥ ችግር አሳሳቢ መሆኑን የሁሉንም ክፍለ ከተሞች መረጃ በመጥቀስ ዝርዝር ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ምንም አይነት የመልካም አስተዳደር ችግር የሌለባቸው መሆናቸውን ተከትሎ ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን በቅንጅት መስራት፣ የማያቀቋርጥ ውይይት በማድረግ ጣልቃ ገብነት መቀነስ፣ ገቢ ማመንጨት እና በራስ አቅም ስራ ማከናወን ችግሮችን ለመቀረፍ የተከተሏቸው መንገዶች መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡ የተሻለ ስራ ለመስራት እንቅስቃሴ የጀመሩ ወጣት ስብእና ማዕከላት ችግሮች ከሥራ አስኪጅ፣ ከወረዳ እና ከክፍለ ከተማ እንዳያልፉ ወጣቶችን ማደራጀት እና ገቢ መፍጠር ወሳኝ መሆኑን በምክረ ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን አዲስ ነገር የመፍጠር አቅማችን ከዳበረ አመራሩን ማሳመን የሚቻልበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ገልጸዋል፡፡

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.