15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ተጀምሯል

መዲናዋ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የአካል ጉዳተኞችን እና መስማት የተሳናቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን የስፖርት ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት በሚያረጋጥ መልኩ የተገነቡ ናቸው። አቶ በላይ ደጀን 15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ተጀምሯል ህዳር 13 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አዘጋጅነት በየካ ክፍለ ከተማ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ተጀመረ ውድድሩን በይፋ ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ሰፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በመዲናዋ ወዲህ የተገነቡ 1530 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የአካል ጉዳተኞቸን እና መስማት የተሳናቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን የስፖርት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ የተገነቡ መሆናቸው ተናግረዋል በመፍጠር፣በመፍጠን እና በመዝለል የከተማችን ብሎም የአገራችንን የስፓርት ትንሳኤ እናረጋግጣለን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የአካል ጉዳተኞች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ዋና ዓላማ በስፖርት ጤንነታቸውን እንዲጠብቁ በማስቻል የእርስ በእርስ ትስስራቸውን ማጠናከር ነው ብለዋል፡፡ አካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው የህብረሰብ ክፍሎች በአገራቸው ሁለንተናዊ ልማት ላይ የመሳተፍ አቅምም ብቃትም አላቸው ያሉት አቶ በላይ ውድድር እኩል፣ፍትሐዊ የሆነ እና የስኬት ዕድል እንዲያገኙ ለማድረግ የዓለም አቀፋ የድልድል ስርዓት (classification) ተግራዊ እንድታደረግ ጥሪ አቅርበዋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቆንጅት ደበላ በበኩላቸው ስፖርት ፌስቲቫሉ አካል ጉዳተኞችን ለማሳተፍና ለማስጠቀም ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸው የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ የስብአዊ የዲሞክራሲያዊ መብት እና የልማት አጀንዳ ውጤታማ ለማድርግ በልዩ ትኩሩት እንዲሰራ ገልጸዋል ዘንድሮ የምናዘጋጀውን የስፖርት ፌስቲቫል ጨምሮ የስፓርት ተድራሽነት ለማስፋት በትኩረት እየሰራን እንገኛለን ያሉት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም ኃይሌ ተወዳዳሪዎች በሚኖራቸው ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ፌስቲቫል እና ውድድሩ ለአካል ጉዳተኞች የውድድር ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር የእርስ በእርስ ትስስርን ያጠናክራል ያሉት የፓራሊምፒክስ ኮሚቴ ፕሬዘዳንት አቶ በቀለ ጎንፋ አካል ጉዳተኞችን ወደ አደባባይ በማውጣት መስራት እንደሚችሉ የምናሳይበት ትልቅ መድረኮች ሊስፋፉ ይገባል ብለዋል፡፡ ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድርና ፌስቲቫል ''አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ስፖርት እድገት'' በሚል መሪ ቃል በ7 የስፖርት አይነት ከሕዳር 13 እስከ ሕዳር 24/2018ዓ.ም እንደሚካሄድ ተመልክቷል፡፡ በመክፈቻ በተካሄደው የወንዶች አይነ ሥውራን የገመድ ጉተታ ውድድር ጉለሌ ክፍለ ከተማ ቂርቆሰ ክፍለ ከተማን 2ለ0 አሸንፏል

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.