በመዲናዋ የሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በመዲናዋ የሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሳተፋበት ስፖርታዊ ውድድር ከግንቦት 10 ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይካሄዳል ።

ግንቦት 06 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመዲናዋ የሚገኙ 2ኛ ደረጃ የሚሳተፉበት ስፖርታዊ ውድድር ከግንቦት 10 እስከ 24/2016 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።

ትምህርት ቤቶች ለሰላም፣ ለአብሮነት እና ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር በሁለቱም ፃታ በስድስት የስፖርት አይነቶች 11ዱም ክፍለ ከተሞች እንደሚሳተፉበት የሁለቱ ቢሮዎች በሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተመላክቷል።

ትምህርት ቤቶች የተተኪ ስፖርተኞች መፍለቂያ ማድረግ እንዲሁም በአእምሮ እና በአካል የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር የውድድሩ ዋነኛ አላማ እንደሆነ የተናገሩት አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ በውድድሩ የተለየ ችሎታ እና ብቃት ያሳዩ ስፖርተኞች በተለያዩ ክለቦች እና ቡድኖች የምልመላ እድል ሊያገኙ የሚችሉበት ውድድር ነው ብለዋል።

በመዲናዋ በሚገኙ የመንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በስፋት እየተካሄዱ ሲሆን ስፖርትን ባህሉ ያደረገ የትምህርት ማህበረሰብ ለመፈጠር የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶቾ እና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ዳ/ር ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ በቀጣይም ትምህርት ቤቶች የተተኪ ስፖርተኞች መፍለቂያ እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ቅዳሜ ግንቦት 10/2016ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ የሚጀመር ሲሆን በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የከተማው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የስፖርት ቤተሰቦች በተገኙበት በደማቅ የመክፈቻ ስነ ስርዓተሰ እንደሚጀመር በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተመልክቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.