የ5ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ ክለቦች አቋም መለኪ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የ5ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ ክለቦች አቋም መለኪያ ውድድር በመቻል አሸናፊነት ተጠናቀቀ ህዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም

የ5ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ ክለቦች አቋም መለኪያ ውድድር በመቻል አሸናፊነት ተጠናቀቀ ህዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክስዮን ማሕበር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 5ኛው ፔፕሲ አዲስ አበባ ክለቦች አቋም መለኪያ አትሌቲክስ ውድድር በመቻል ስፓርት ክለብ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለተከታታይ አራት ቀናት ሲካሄድ የቆየውን ውድድር በ437 ነጥብ መቻል ሻምፒዮና ሲሆን በ355 ነጥብ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ሲያጠናቅቅ ኢኮስኮ በ67 ነጥብ ሦስተኛ ሆኗል በሴቶች መካከል በተካሄደ ውድድር 200 ነጥብ የሰበሰበው መቻል የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን ኢትዮ ኤሌክትሪክ 173 ነጥብ ሁለተኛ ኦሜድላ በ29 ነጥብ ሦስተኛ ሆኖ አጠናቋል በወንዶች በተካሄደው ውድድር 237 መቻል የውድድሩ ሻምፒዮና ሲሆን 184 ነጥብ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 2ኛ በ37 ነጥብ ኢኮስኮ ሦስተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቌል ውድድሩ ለተተኪ ስፖርተኞች የውድድር ልምድ እንዲያገኙ እድል እንደሚሰጥ የገለጹት የፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ ለታሳታፊ ክለቦች ምስጋና አቅርበዋል በውድድሩ ከ18 ክለቦች የተውጣጡ ከ370 በላይ አትሌቶች መሳተፋቸውን ያስታወሱት የፌደሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ተስፋዬ ለተከታታይ አራት ቀናት በተካሄደው ውድድር ክለቦች በሜዳ ላይ ተግባራት፣ በአጭር እና በረጅም ርቀት ከፍተኛ ፉክክር ማድረጋቸው ገልጸዋል በርዝመት ዝላይ፣በስሉስ እና ከፍታ ዝላይ ሦስት የወርቅ ሜዳልያ ያስመዘገበችው የመቻሏ በጸሎት አለማየሁ የማረታቻ ሽልማት ሲበረከትላት አሰልጣኟ ሰለሞን በንቲ የኮከብ አሰልጣኝነት እውቅና ተችሯታል በአሰልጣኝ ጌታቸው ሙሉጌታ የሚሰለጥነው አትሌት ሃብታሙ ሐጎስ፣ በ110 ሜትር፣ በ400ሜትር እና 4*400 አጭር ርቀቶች የሦስት የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት በመሆኑ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.