"በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ!" በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ለልዩ ወረዳ ሴክተር ተቋማት
"በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ!" በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ለልዩ ወረዳ ሴክተር ተቋማት አባላት "በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ ! " በሚል ርዕስ ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና በፓርቲያችን የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ተጠቃልሏል። ስልጠናው የብልፅግንና ጉዞ ለማፋጠን ተጨማሪ አቅም የሚሆኑ ጥልቅ እሳቤዎች እና ተጨባጭ ተግባራት ተሰናስነው የቀረቡበት መሆኑ ተገልጿል። የግብርና እና ገጠር ልማት ትራንስፎርሜሽን እንዲሳካ የገጠር እና የከተማ ትስስርን ለማጠናከር የተጀማመሩ አበረታች ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ተጠቁሟል ። ቱሪዝምን ሀገራችን ማግኘት ያለባትን እንድታገኝ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር እና ለመደመር ትውልድ ግንባታ ለማዋል እየተደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ ርብርብም በስልጠናው ተጠቃቅሷል። በስልጠናው "በመደመር መንግስት እይታ የቱሪዝም እና የከተማ ልማት እመርታ " በሚል ርዕስ ከተሜነትን እና ቱሪዝምን ለማስፋፋት በተለያዩ ስርዓቶች የተሞካኮሩ ጥረቶች እንዲሁም ከዘመኑ ጋር አብሮ መራመድ ባለመቻሉ የገጠሙ ተግዳሮቶች ፣ ብልፅግና ፓርቲ በተለወጠ አስተሳሰብ ፣ በዳበረ የስራ ባህል እያስመዘገባቸው የሚገኙ እመርታዎች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው በውይይት ዳብረዋል። ከተሞች የብልፅግናችን መዳረሻ በመሆናቸው በዕቅድ ፣ በስትራቴጂ እና በብቃት መምራት እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን አባላት አገልግሎት አሰጣጥን በማሳለጥ ፣ ህገወጥነትን በመከላከል ፣ አሰባሳቢ ገዥ ትርክትን በመገንባት ፣ የተቀናጀ ዘመናዊ መሰረተ ልማት እንዲዳረስ የድርሻን በመወጣት፣ አረንጓዴ ፣ ፅዱና ስሉጥ ከተማ ግንባታውን ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸው ተመላክቷል። ብዝሀ ኢኮኖሚን ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው ብልፅግና ፓርቲ ለቱሪዝም ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት በአግባቡ በመረዳት በየአካባቢው የሚገኙ የቱሪዝም ፀጋዎችን በማልማት ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን በመጠበቅ በመንከባከብ፣ ሀገራዊ የእንግዳ ተቀባይነት እሴትን በማጎልበት አባላት ግንባር ቀደም ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተገልጿል። የግብና እና ገጠር ልማት ትራንስፎሜሽኑን ውጤታማነት በማጉላት ለኢንዱስትሪው አስፈላጊውን ግብዓት ለማሟላት እንዲሁም ግብርናውን በኢንዱስትሪ ምርቶች እና በቴክኖሎጂ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እንደ ሀገርም እንደ ከተማችንም እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትም ተነሳሽነትን በሚያሳድግ መልኩ ለአባላት ቀርበዋል። የተጀመረው አጓጊ ልማት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና መዳረሻችን የሆነው ሁለንተናዊ ብልፅግና ዕውን እንዲሆን በየተሰማሩበት ተቋማዊ አቅምን በማዳበር ፣ አገልግሎት አሰጣጡ እንዲቀላጠፍ ድርብርብር ተልዕኳቸውን ለመወጣት ብርቱ ርብርብ ለማድረግም አባላት ተግባቦት ፈጥረዋል። በመጨረሻም ሰልጣኝ አባላት የከተማችንን ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በመጎብኘት በስልጠናው ካገኟቸው ዕውቀቶች በተጨማሪ አቅማቸውን ገንብተዋል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.