በመፍጠር፣ በመፍጠን እና በመዝለል በሀገራችንን...

image description
- ውስጥ supporter    0

በመፍጠር፣ በመፍጠን እና በመዝለል በሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ሁሉም አካል አሻራውን ሊያስቀምጥ ይገባል። አቶ በላይ ደጀን

በመፍጠር፣ በመፍጠን እና በመዝለል በሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ ሁሉም አካል አሻራውን ሊያስቀምጥ ይገባል። አቶ በላይ ደጀን ህዳር 30 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ቀናት በሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ልዩ ወረዳ የብልፅግና ፖርቲ አባላት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ። ስልጠናዋው በመደመር መንግስት እይታ የግብርና የገጠር የማዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ተካሂዷል። በስልጠናው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊና የልዩ ወረዳው ሰብሳቢ አቶ በላይ ደጀን ስልጠናው በአመራሩና በአባሉ ዘንድ በሀገራዊ አጀንዳዎች የጠራ አመለካከት ለመፍጠር እና ተቀራራቢ እውቀት እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል በመደመር እሳቤ በመፍጠር፣ በመፍጠን እና በመዝለል ለሀገራችን የብልፅግና ጉዞ ሁሉም አካል አሻራውን ሊያስቀምጥ እንደሚገባ አቶ በላይ አሳስበዋል። ከተማንና ከተሜነትን ማስፋፋት፣ የኢንዱስትሪ ዘርፋን ማዘመን እና የቱሪስት መስህብነትን እንደ ከተማ ብሎም እንደ ሀገር ማሳደግ እንደሚገባ በስልጠናው ላይ በዝርዝር ተመላክቷል። በቀጣይ እንደ ሀገር መንግስት ትኩረት በማያደርግባቸው ጉዳዮች ላይም አቅጣጫ ተሰጥቷል። በስልጠናው መጨረሻም አባሉ በከተማዋ የተገነቡ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.