ባለሙያዎች ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በ...

image description
- ውስጥ supporter    0

ባለሙያዎች ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ስራ ሚናቸው መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ

ባለሙያዎች ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ስራ ሚናቸው መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ

ታህሳስ 1 2018 ዓ/ም ወጣቶችን ስፖርት ቢሮ

ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ በሚደረገው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ውስጥ በሁሉም የስራ መስክ የተሰማሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ባለሙያዎች የጎላ ሚና መጫወት እንዳለባቸው ተገለጸ

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን በአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በኢትዮ በፕሮግራሚንግ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በዳታ ሳይንስ፣አንድሮይድ ልማት እና ኪው አር ኮድ አጠቃቀም ላይ የሚያተኩር ስልጠና ለቢሮ ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡

በዲጂታል ክህሎት የበለጸገ ባለሙያ የሀገሪቱን ዲጂታል ሽግግር ለማገዝ ትልቅ አቅም እንደሚሆን የገለጹት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድ መሪ አቶ መሸሻ ደመቀ ለቴክኖሎጂ እና ለኢኖቬሽን ዋጋ የሚሰጥ ባለሙያ ወቅቱ እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ወደ 30ሺ የሚጠጉ የከተማ ወጣቶች ኮደርስ ስልጠና እንሰለጥኑ ዕቅድ መያዙን ያመላከቱት አቶ መሸሻ በተቋሙ የሚገኙ ባለሙያዎች የቴክኖሎጂ መሰረታዊ እውቀታቸውን በማዳበር ዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለመሆን የኮዲንግ ስልጠና ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ በማድረግ በኪአር ኮድ የደንበኞች አገልግሎት እርካታ እየተለካ እንደሚገኝ ያስታወሱት አቶ መሸሻ የመለወጥ አቅምን በማዳበር አዳዲስ አሰራሮችን የመቀበል እና ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት ከባለሙዎች እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

የተሰጠው ስልጠና በኮዲንግ ስልጠና ላይ በንቃት እንዲሳተፉ በማድረግ ክህሎታቸውን ያዳበረ መሆኑን የገለጹት የስልጠናው ተሳታፊዎች በስማርት ከተማ ግንባታ ውስጥ እንደ ባለሙያ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.