አገርን በዓለም መድረክ የሚወከሉ ስፖርተኞችን ለ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

አገርን በዓለም መድረክ የሚወከሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት የስፖርት ልማቱን የሚያፋጥኑ ባለሙያዎች ማፍራት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

አገርን በዓለም መድረክ የሚወከሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት የስፖርት ልማቱን የሚያፋጥኑ ባለሙያዎች ማፍራት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ ታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በስፖርት ዘርፍ ከክፍለ ከተማ እስከ ከተማ ለሚገኙ ለስፖርት ማህበራት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ የስፖርት ልማትን ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀው ስልጠና በማስጠልኛ ተቋማት አመሰራረት፣ ስታንዳርድ፣ የስልጠና ሽግግር እና ምዘና የስልጠና እቅድ ይዘቶች የሚያተኩር መሆኑን የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡ ተወዳዳሪ እና አገርን የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የስፖርት ዘርፍ ባለሙያዎች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው የገለጹት የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ ከተማ አስተዳደሩን በሁሉም የስፖርት ዲሲፕሊን ውጤታማ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎቸ ተጠናክረው አንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ በስፖርቱ ዘርፍ ላሉ ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በስፋት እየተሰጠ እንደሚገኝ ያወሱት አቶ ጎሳዬ ተተኪዎችን በብዛት እና በጥራት ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የስፖርት ያላቸውን ሚና አመላክቷል፡፡ በአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በተሰጠው ስልጠና ላይ የማሰልጠኛ ተቋማት አመሰራረት፣ የሰልጣኝ እድሜ ደረጃ እና የቆይታ ግዜ በየስፖርት አይነቱ፣ የስፖርት ማሰልጠኛ ተቋማት ስታንዳርድ፣የፋሲሊቲ እና የስልጠና ስታንዳርድ፣ የስልጠና ሽግግር እና ምዘና እና የስልጠና እቅድ ይዘቶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰቷል

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.