ቢሮው የፀረ ሙስና ትግልን ውጤታማ ለማድረግ ላበ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ቢሮው የፀረ ሙስና ትግልን ውጤታማ ለማድረግ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ እውቅና ተበረከተለት።

ቢሮው የፀረ ሙስና ትግልን ውጤታማ ለማድረግ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እውቅና ተበረከተለት። ታህሳስ 03 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የፀረ ሙስና ትግልን ውጤታማ ለማድረግ ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እውቅና ተበርክቶለታል። ቢሮው እውቅና የተበረከተለት ኮሚሽኑ 22ኛው የአለም የፀረ ሙስና ቀን የማጠቃለያ ውይይት ባደረገበት ወቅት ሲሆን እውቅናውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እጅ ተቀብለዋል። ሙስናን የሚጠየፍና አምርሮ የሚታገል ትውልድ ለመፍጠር እንደከተማ ብሎም እንደሀገር የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ቢሮው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ከመስጠት ጀምሮ ውጤታማ እንቅስቃሴ እያካሄደ መሆኑ ተመላክቷል። የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ሙስና ኮሚሽን 22ኛውን የአለም የፀረ ሙስና ቀንን በተለያዩ ሁነቶች ሲያከብር በርካታ የከተማዋ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች የተሳተፋበት ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀ ግብር እንዲካሄድ ቢሮው አበሮክቶው ከፍተኛ እንደነበር ተገልፆል።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.