የከንቲባ ፅ/ቤት የድጋፍና ግምገማ ዘርፍ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ደንብ አተገባበር ባካሄደው ኢንስፔኬሽን ሪፖርት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
የከንቲባ ፅ/ቤት የድጋፍና ግምገማ ዘርፍ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ደንብ አተገባበር ባካሄደው ኢንስፔኬሽን ሪፖርት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ። ታህሳስ 03 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የድጋፍና ግምገማ ዘርፍ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ደንብ ቁጥር 189/2017 አተገባበር ባካሄደው ኢንስፔክሽን ሪፖርት ዙሪያ ውይይት ከዘርፉ አመራርች ጋር ውይይት አድርጎል። በውይይቱ ላይ የከንቲባ ፅ/ቤት የድጋፍና ግምገማ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሞላ ንጉስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ስራአስኪያጆች ተገኝተዋል። ኢንስፔክሽን ቡድኑ በ9 ክፍለ ከተሞችን የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን እና የራስ ሀይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከልን ምልከታ ማድረጉን በሪፖርቱ አመላክቷል። በሁሉም ክፍለ ከተሞች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ለታዳጊዎች፣ ለወጣቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአከባቢው ማህበረሰብ ቅድሚያ የሚሰጡበት አሰራር መኖሩ፣ በየክፍለ ከተማው የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መረጃ ተደራጅቷ መያዙ እና ሜዳዎችን የሚከባከቡ፣ የሚጠብቁ ሰዎችን በቅጥር እንዲሞላ መደረጉ የኢንስፔክሽን ቡድኑ በጥንካሬ አስቀምጧታል። በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አስተዳደር ደንብ ቁጥር 189/2017 ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ መፍጠር በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች መሰራቱ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ገቢ እንዲያመጩ ከማድርጎ አኳያ ክፍተት መኖሩ፣ ተመርቀው ወደ ስራ ያልገቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መኖራቸው በኢንስፔክሽን ቡዱኑ በምልከታው በክፍተት ያስቀመጣቸው ናቸው። ኢንስፔክሽን ቡድኑ በቀጣይ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ያላቸውን ጉዳዮች በሪፖርቱ ያመላከተ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በጥንካሬ የተመላከቱ ተግባራትን በማስቀጠል በክፍተት የታዩትን በፍጥነት በማረም የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አተገባበር ደንብን መቶ ፐርሰንት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ ቢሮው በትኩረት እንደሚሰራ አሳውቀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.