
ቢሮው በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሙሉ እድሳት የተደረገለትን የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከልን ተረከበ።
ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ የኢፌድሪ ሥራ እና ክህሎት ሚንስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ሙሉ እድሳት ያደረገለትን የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የወጣት ስብዕና ማዕከልን ተረከበ።
በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባስተላለፋት መልዕክት ወጣቶችን በአካል በአእምሮ ለመገንባት ከተማ አስተዳደሩ 113 ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ሞዴል ለማድረግ እየተሰራ ላለው ስራ ዛሬ የስራና ክህሎት ሚንስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ሙሉ እድሳት ያደረገለት ማዕከል ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
ማዕከላቱን ከመገንባት ባሻገር ለወጣቱ የሚመጥን እንዲሆኑ በሰው ኃይል ማደራጀት በቴክኖሎጂ ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት አቶ በላይ ማእከላቱን ሳቢ እና ማራኪ ለማድረግ በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው በዘርፉ የሚሰራውን ስራ ለማጠናከር የግል ባለሃብቶችንና የልማት ድርጅቶችን ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርዋል
በርክክብ ወቅት የተገኙት የስራና ክህሎት ሚንስቴር የስራ ስምሪትና ገባያ ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ወጣት ስብዕና ማዕከላት ወጣቶች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ለአገር ብልጽግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገለጸው ስራዎች በማዘመን ለሌላው ተሞክሮ የሚወሰድበት ተቋም እንደሆነ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ማዕከሉ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የዲዛይን ስራ በማሻሻል ሙሉ እድሳት እንደተደረገለት ያወሱት ሚንስቴር ዲኤታው በወጣት ማዕከሉ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ስዒድ አሊ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ስራ ፈላጊ ወጣቶች በማደራጀት ህይወት እንዲለውጡ ከማደረጋቸው በላይ በዝንባሌያቸው የሚሰለጥኑበት መሆኑን ገልጸዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.