በመዲናዋ በሚገኙ 119 ወረዳዎች "የጉባ ብስራቶ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በመዲናዋ በሚገኙ 119 ወረዳዎች "የጉባ ብስራቶች ፤ የመደመር መንግስት ቱሩፋቶች" በሚል መሪ ሀሳብ፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙርያ ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ።

በመዲናዋ በሚገኙ 119 ወረዳዎች "የጉባ ብስራቶች ፤ የመደመር መንግስት ቱሩፋቶች" በሚል መሪ ሀሳብ፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙርያ ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ። በልማት እና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ ከዚህ በፊት በማዕከል እና በክፍለ ከተማ ደረጃ ህዝባዊ ውይይቶች መደረጋቸው የሚታወስ ነው። በዛሬው እለት ደግሞ በመዲናችን በሚገኙ በ119 ወረዳዎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በልማት እና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ዙርያ ውይይ ተካሂዷል። በውይይ መድረኩ ላይ ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች አዳምጦ ተገቢ ምላሽ መስጠት የብልፅግና ፓርቲ መገለጫ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ባለፉት የለውጥ አመታት መንግስት ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ በመስራቱ የኢትዮጲያን ከፍታ የሚያረጋግጡ ስኬታማ ስራዎች ተከናውነዋል ተብሏል። በዚህም የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ስራዎች በመስራት አዲስ አበባ ከተማን የዓለም የስህበት ማዕከል፣ ለነዋሪዎቿ ውብና ፅዱ ከተማ እንዲሁም የዓለም የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ከተማ ማድረግ ተችሏል ተብሏል። እነዚህ በለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ሰፋፊ ስኬቶች ህዝብና መንግስት ተመካክረው በመስራታቸው የመጡ ውጤቶች መሆናቸውንም በውይይቱ ተገልፃል። የዛሬው የውይይት መድረክ ዓላማም ከህዝብ ጋር በመወያየት የሚነሱ ሀሳብና አስተያየቶችን ለቀጣይ እቅድ እንደመነሻ በመጠቀም ለሀገራችን ከፍታ ከህዝብ ጋር በቅንጅት ለመስራ እንደሆነም ተመላክቷል። በአዲስ አበባ ከተማ ከማህበረሰቡ ለሚነሱ ለልማት እና ለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥም ተገልፃል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.