ከአምስት ክለቦች የተውጣጡ ከ200 በላይ ብስክሌ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ከአምስት ክለቦች የተውጣጡ ከ200 በላይ ብስክሌተኞች የተሳፉበት የአቋም መለኪያ ውድድር እንደቀጠለ ነው ታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

ከአምስት ክለቦች የተውጣጡ ከ200 በላይ ብስክሌተኞች የተሳፉበት የአቋም መለኪያ ውድድር እንደቀጠለ ነው ታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብስክሌት ፌዴሬሽን ያዘጋጀው ከአመስት ክለቦች የተውጣጡ ከ200 በላይ ብስክሌተኞች የተሳፉበት የ2018 ዓ/ም የአቋመ መለኪያ የብስክሌት ውድድር እንደቀጠለ ነው በውድድሩ ክለቦች፣ታዳጊዎች፣ የግል ተወዳዳሪዎች የቀድሞ ብስክሌተኞች እና ቡድኖች የሚሳተፉበት መሆኑን የገለጹት የፌደሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ተረፈ ውድድር የኮሪደር ልማት የብስክሌት ጎዳናዎች የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማስፋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአቋም መለኪያው ውድድሩ ክለቦችና ስፖርተኞች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ያስችላቸዋል ያሉት አቶ ሲሳይ አዲስ አበባ ወክለው በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሳተፉ ስፖርኞችን ለመምረጥ የሚያስችል ውድድር መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ በማውንቴን ታዳጊ ሴቶች 13.6 ኪሎ ሜትር በሸፈነ ውድድር ሀና ተሻለ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ አሳንቲ ቦሪ እና ቤተልሄም ተስፉዬ 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ በማውንቴን አዋቂ ሴቶች 13.6 ኪሎ ሜትር በሸፈነ ውድድር ሀዊ ደሪባ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ አስቴር መገርሳ እና ሮማን አቢዮት ተከታትለው ገብተዋል በኮርስ አዋቂ ሴቶች 24.8 ኪሎ ሜትር በሸፈነ ውድድር ማርታ ካሳሁን 1ኛ ሌሎ ሁንዴ 2ኛ ማለፊያ ሽፈራው 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡ በማውንቴን ታዳጊ ወንዶች 17 ኪሎ ሜትር በሸፈነ ውድድር ሚሊዮን ብዙነህ ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅ ያሬድ መላኩ እና ኩመላ ቀልቤሳ ተከታትለው ገብተዋል በማውንቴን አዋቂ ወንዶች 24.8 ኪሎ ሜትር በሸፈነ ውድድር ጴንኤል አባተ ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅ አሜን ጀምበሩ እና ሀቢብ ሀይደር በቅደም ተከተል 2ኛ እና 3ኛ ሆነው ጨርሰዋል፡፡ በክለቦች ውድድር የአእምሮ መንግስቱ ከ.አ ፖሊስ ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ዮሀንስ ታሪኩ ከሸገር እና ሙደሲር አስራት ከአካዳሚ ተከታትለው ገብተዋለል በእለቱ በኮርስ ውድድር ከ1-3 ለወጡ አሸናፊዎች የብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.