የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው አካሄደ። ታህሳስ5 ቀን 2018 ዓ.ም
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው አካሄደ። ታህሳስ5 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስፖርትአስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት 17ኛን ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላትና የክብር እንግዶች በተገኙበት ተካሄዷል። በጉባኤው የ2017 ዓ.ም የምክር ቤቱ ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት የስራ እቅድ እና የምክር ቤቱ የ2017 ዓ.ም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡ መንግስት ለስፖርት ዘርፉ በሰጠዉ ትኩረት የወጣቶች ማዘውተሪያና የህጻናት መጫወቻ ቦታዎችን እያለማ እንደሚገኝ የገለጹት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሩ መንግስቱ በስፖርት የዳበረ ጤናማ ትዉልድ ለመገንባት እየተራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ተክሌ በበኩላቸው ክፍለ ከተማው በተካሄዱ ከተማ አቀፍ ውድድሮች ውጤታማ መሆኑን አውስተው በመንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ የሚገኘውን ስፖርት ለማጠናከር የክፍለ ከተማዉ ባለሀብቶች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅረበዋል፡፡ በቀረበው ሪፖርትና ዕቅድ ሀሳብ የሰጡ ተሳታፊዎች እንደጠቀሱት የእግር ኳስ ቡድኑ ህዝባዊ መሰረት መያዝ አለበት በማለት ለሌሎች ስፖርት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማስፋፋት ህጻናትና ታዳጊዎች አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ የስፖርት ዘርፍን ማጠናከር ይገባል በማለት የታዳጊ ፕሮጀክቶችን በትምህርት ቤቶች ማስፋፋት እንዳለበትም ተጠቁሟል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.