በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ ) እጅ ኳ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ ) እጅ ኳስ ውድድር በወንዶች መቻል በሴቶች እሸት ሻምፒዮና ሆኑ ታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ ) እጅ ኳስ ውድድር በወንዶች መቻል በሴቶች እሸት ሻምፒዮና ሆኑ ታህሳስ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የ2018 ዓ.ም የእጅ ኳስ ሲቲ ካፕ የክለቦች ውድድርን በወንዶች መቻል በሴቶች በእሸት አሸናፊነት ተጠናቀቀ በትንሸዋ ስቴድየም ለተከታታይ 15 ቀናት ሲካሄድ በቆየው ውድድር በወንዶች መቻል ሻምፒዮና በመሆን ዋንጫ እና የወርቅ ሜዳልያውን ከማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት የግሉ ሲያደርግ ኦሜድላ የብር ሜዳልያ ቂርቆሰ ክፍለ ከተማ የነሐስ ሜዳልያ ባለቤት ሆነዋል፡፡ ሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፉበት ውድድር በታዳጊዎች የተገነባው እሸት ክለብ የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሲሆን ፊንሐንስ እና ኮልፌ ፊንሃንስ በቅደም ተከተል የብር እና የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የእጅ ኳስ ስፓርትን ለማስፋፋት እና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ያሉት የፌድሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ሳሙኤል ንጉሱ የዘንድሮው ሲቲ ካፕ ውድድር ላይ ክለቦች በሁለቱም ጾታ መሳተፋቸው ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ ለኮከብ ዳኛ፣ ለኮከብ አሰልጣኝ እና ለኮከብ ተጫዎች የማበረታቻ ሽልማት ከመስጠቱ ባሻገር ውድድሩን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ላጠናቀቁ ክለቦች የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል፡

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.