በኮሪደር ልማቱ ከፒያሳ አከባቢ ተነስተው ንፋስ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በኮሪደር ልማቱ ከፒያሳ አከባቢ ተነስተው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የገቡ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች አራዳ ፖርክን ጎበኙ።

በኮሪደር ልማቱ ከፒያሳ አከባቢ ተነስተው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የገቡ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች አራዳ ፖርክን ጎበኙ። ታህሳስ 05 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በኮሪደር ልማት ከፒያሳ አከባቢ ተነስተው ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ የገቡ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች አራዳ ፓርክን ተዘዋውረው ጎበኙ። በአራዳ ፓርክ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ያስጎበኙት የወንዝ ዳርቻና እና የኮሪደር ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ከደር አደም ሲሆኑ ፖርኩ በ42 ሄክተር መሬት ላይ ያረፈና በውስጡ የስፖርት አሬና፣ የልጆች መጫዎች ስፍራዎች፣ አፊ ቲያትሮች፣ የስብሰባ አደራሾች፣ የመኪና መቆሚያዎች፣ ሱቋች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የመሮጫ ትራኮች፣ የብስክሌት መንገዶችን ጨምሮ አንድ ትንሽ ከተማ ሊኖራት የሚችል መሰረተ ልማቶችን በአንድ ቦታ አካቶ የተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ጎብኝዎቹ ከዚህ በፊት ይኖሩበት የነበረው የፒያሳ አከባቢ በኮሪደር ልማቱ ለምቶ በማየታቸው እንዲሁም የልማቱ አንድ አካል እና ተጠቃሚም በመሆናቸውን መደሰታቸውን ገልፀዋል። ከዚህ በፊት ሲኖሩበት የነበረው ፒያሳ አከባቢ ለመኖር ምቹ ያልነበረና ለብዙ እንግልት ሲዳረጉ እንደነበረ ያስታወሱት ጎብኝዎቹ ከተማ አስተዳደሩ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ያመቻቸላቸው መኖሪያ ቦታ እና በአከባቢው የተሰሩ የልማት ስራዎች ኑሯቸውን ደስተኛና ቀላል እዳረገላቸው አያይዘው ተናግረዋል። በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በአራዳ ፓርክ የተሰሩ የልማት ስራዎች የሀገርን መልካም ገፅታ የሚገነቡ፣ አዲስ አበባን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት መሆኗን የሚያሳዩ ተጨማሪ ገፀ በረከቶች ናቸው ብለዋል። በፓርኩ ላይ የተሰሩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራውች፣ የልጆች መጫወቻ ቦታዎች፣ አፊ ቲያትሮች እና መዝናኛ ቦታዎች መንግስት ለነገ ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች እና ወጣቶች የሰጠውን ልዩ ትኩረት ያሳያል ሲሉ አቶ በላይ ተናግረዋል። በልማት ምክንያት ከኮሳችስ ጨምሮ ከተለያዩ ቦታዎች አከባቢዎች ተነስተው ውደ ሌላ ቦታ ገቡ ነዋሪዎች በቀጣይ በተነሱበት አከባቢ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እንዲጎበኙ እንደሚደረግ የቢሮ ሀላፊው አሳውቀዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ ከፒያሳ አከባቢ በልማቱ ተነስተው ወደ ክፍለ ከተማቸው የመጡ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤት ከማመቻቸት ጀምሮ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች እየተሞላላቸው መሆኑን ተናግረዋል በቅርቡም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ነዋሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረው መመልከታቸውን እና በአከባቢያቸው የተሰሩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረገቸውን ገልፀዋል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.