ቢሮው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መድረኩን...

image description
- ውስጥ supporter    0

ቢሮው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መድረኩን አካሄደ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ቢሮው የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መድረኩን አካሄደ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የሰኞ የእውቀት ሽግግር መድረክን ወርቃማ በሕይወት ደስተኛ ለመሆን በሚያስችሉ አስር ነጥቦች ዙሪያ ውይይት አካሄደ ዘውትር ሰኞ እየተካሄደ የሚገኘው የዕውቀት ሽግግር መድረክ የስራ ተነሳሽነትን እየፈጠረ እንደሚገኝ የገለጹት የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ አዳዲስ ሃሳቦችን በመጨመር የህይወት ልምድ የምንለዋወጥበት መድረክ በመሆኑ በጠንካራ ቅድመ ዝግጅት ገነቢ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች መካሄድ እንዳለበት አሳውቀዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው አማካሪ አቶ ታሪኩ እሸቴ በበኩላቸው አመራሩ እና ባለሙያው ውጤታማ ስራ እየሩ እንደሚገኝ ገልጸው ወርቃማ ልምዶቻችንን የምናጋራበት የወርቃማ ሰኞ የዕውቀት ሽግግር መድርክ ተቋማዊ አብሮነትን ለማጠናከር እንደሚረዳ ገልጸዋል ደስተኛ ለመሆን የሚረዱ አስር ነጥቦች በሚል ባዘጋጁት ርዕስ ላይ ገለጻ ያደረጉት የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ ፈለቀ ዋቄ በሕይወታችን ደስተኛ ለመሆን በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ የስራ ክህሎታችን በማዳበር በሥራ ገበታ ላይ ደስተኛ መሆን እንደሚቻል ያመላከቱት አቶ ፈለቀ በህይወታችን ደስተኛ የሚያደርጉን ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡፡

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.