ከሱስ የተላቀቀ ጤናማ እና አምራች ዜጋን በመፍጠር የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን። አቶ በላይ ደጀን
ከሱስ የተላቀቀ ጤናማ እና አምራች ዜጋን በመፍጠር የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን። አቶ በላይ ደጀን ታህሳስ 07 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኦሳድ ከተሰኝ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ለወጣቶች የሱስ ተጋላጭነትና አስከፊነት ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው መክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ወጣቶችን ሁለንተናዊ ስብዕና የሚገነቡ ምቹ፣ ፅዱና ዘመናዊ የሆኑ 114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በከተማ አስተዳደሩ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ወጣቶች ከሱስና ሴሰኝነት እንዲላቀቁ እንዲሁም ከመጤናና ከጎጂ ባህላዊ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ በሁሉም የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ተከታታይነት ያለው ስልጠና እንደሚሰጥ ገልፀዋል። ከሱስ የተላቀቀ ጤናማ እና አምራች ዜጋን በመፍጠር የኢትዮጵያን የብልፅና ጉዞ እውን ለማድረግ ቢሮው ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አቶ በላይ ተናግረዋል። በሱስ ተጋላጭነት እና አስከፊነት ዙሪያ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና እና ተያያዥነት ያለው ህክምና ዶክተር የሆኑት ዳ/ር ሰለሞን ደቪ ለወጣቶች ስልጠና የሰጡ ሲሆን የሱስ ባህሪያት፣ የሱስ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችና የሱስ ማገማየ ህክምናዎች ላይ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል። በስልጠናው ከዚህ በፊት የተለያዩ ሱሶች ተይዞ የነበረና አሁን ከሱስ ተላቆ የተለያዩ ውጤታማ ስራ እየሰራ የሚገኝው ወጣት ዮናታን ተሞክሮውን ለወጣቶች አካፍሏል። በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ወጣቶች ከሱስ እራሳቸውን በማራቅ ለሀገራችሁ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.