የሀረሪ ክልል እና የሸገር ከተማ ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ጋር ውይይት አካሄዱ።
የሀረሪ ክልል እና የሸገር ከተማ ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ጋር ውይይት አካሄዱ። ታህሳስ 13 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የሀረሪ ክልል አና የሸገር ከተማ ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ጋር ውይይት አካሄዱ። በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ለመወያየት ከሀረሪ እና ከሸገር ከተማ የመጡ ወጣቶችን እንኳን ወደ ህብረ ብሔራዊት የሰላም የአብሮነትና የብልፅግና ተምሳሌት ወደ ሆነችው አዲስ አበባ ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል። አዲስ አበባ በአገራችን በሁሉም ክልል ከሚገኙ የገነባችው የሰላም እሴት ምሳሌ መሆኑን የገለጹት አቶ በላይ የሰላም መኖር ለአገር ልማት እና እድገት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የተጀመሩ የሰላም ግንባታ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ያመላከቱት አቶ በላይ ወጣቶች ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ባሏቸው የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ወንድማማችነትን ማጠናከር ይገባል ብለዋል የተረጋጋ ሰላም እንዲፈጠር ከሃረር ከተማ ብዙ ተሞክሮ መውሰድ ይቻላል ያሉት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር-ዓለም ደምሴ የሰላም አደፍራሽ ሁኔታዎችን ቀድሞ ለመከላከል ወጣቶች ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ የሃረሪ ከተማ ጥንታዊነት በመጥቀስ በሰላም ግንባታ ላይ የነበራትን ሚና ያወሱት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ ፕሬዘዳንት መለስ አባተ የሁሉም ክልል ወጣቶች በአንድ መድረክ መገናኘት ተሞክሮ እና ልምድን እንደሚያዳብር ገልጸዋል የሌይመን እና እናቷ አረጋውያን መርጃ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሌይመን ጂልቢ በበኩላ የሃረር ትንሿ ኢትዮጵያነት ምሳሌ በማድረግ በርካታ የበጎ ፍቃድ ስራ እየሰራች እንደሚደረግ አውስታ መልካምነትን ፍቅርን በማስፋት ሰላምን ዋጋ ከፍለን ማጽናት አለብን ብለዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.