የመደመር ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የአመራሮችና ሰራተኞች ስፖርታዊ ውድድር መካሄድ ጀመረ
የመደመር ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የአመራሮችና ሰራተኞች ስፖርታዊ ውድድር መካሄድ ጀመረ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የመደመር ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የፌደራል እና የአዲስ አበባ አመራሮችና ሰራተኞች ስፖርታዊ ውድድር መካሄድ ጀመረ የመደመር መንግስት ስፖርት፣ ለዲፕሎማሲ ፣ኀብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እና የስፖርት ቱሪዝምን ለማበረታታ እንሚጠቀም ያስታወሱት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ የስፖርት መሰረት ልማትን በማፋጠን ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማስፋፋት አዲስ አበባ ከተማ እያከናወነ ያለው ተግባር እንደሚበረታታ ገልጸዋል፡፡ እንዲህ አይነት ውድድሮች ወንድማማችነትን እና እህትማማችንት ከማጠናከር ባሻገር ጤናማ አመራርና ባለሙያ ለመፍጠር ያስችላል ያሉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛት እና በጥራት ለማፍራት በየደረጃው የሚደረጉ ውድድሮቸ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ለስፖርት ልማቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለጹት ሚንስቴር ዲኤታው አካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህል ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ዛሬ በመክፈቻው በተካሄ የእግረ ኳስ ውድድር አዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ወጣቶች ክንፍ አመራሮች የፌደራል ብልጽግና ክንፍ አቻውን 4 ለ1 በሆነ ሰፊ ልዩነት ማሸነፍ ችሏል፡፡ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ብልጽግና ክንፍ ከፌደራል ወጣቶች ክንፍ ሁለት ጋር ያደረጉት ጨዋታ በአዲስ አበባ ወጣቶች ክንፍ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በገመድ ጉተታ በተካሄደው ውድድር የፌደራል ብልጽግና ክንፍ አዲስ አበባ አቻውን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.