ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ከ500ሺ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ከ500ሺ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ እንደሚካሄድ ተገለጸ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በመተባበር ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ከ500ሺ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ እንደሚካሄድ ተገለጸ በሰላም ዕሴት ግንባታ ዙሪያ የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶች የሚሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ ከብሎክ እስከ ማዕከል እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት የዘርፍ አመራሮች በተገኙበት በተካሄደው መድረክ ላይ ተገልጽዋል፡፡ የኢትዮጵያ እሴት መገለጫ የሆኑትን ባህሎች ሁሉ መጠበቅ ከወጣቱ እንደሚጠበቅ ያመላከቱት የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ የመድረኩ ዓላማ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝ እንዲሆን ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው ብለዋል፡፡ ከፊታችን የሚከበረው የጥምቀት በዓል ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በሚደረገው የውይይት መድረክ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ ያሳሰቡት ወይዘሮ ሊዲያ በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ የሚገኙ የሰላም ግንባታ ስራዎች ጥልቅ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅረበዋል፡፡ በምክንያት የሚያምን በምክንያት የሚደግፍ ወጣት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የዘርፍ አመራሮች ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በዓሉ በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ እንዲከበር በቅንጅት ሲሰራ የቆየው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ ወጣቶች ቀርበን ካወያየናቸው በአገራችን ብሎም በከተማ አስተዳደሩ እድገት እና ልማት ላይ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ቁርጠኛ ናቸው ያሉት አቶ በላይ እና የከተማችን ዘለቄታዊ ሠላም ለማረጋገጥ አንድነታችንን ለማስቀጠል እንዲህ አይነት ውይይት ጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል በዘተጋጀው የንቅናቄ እቅድ ላይ ገለጻ ያደረጉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብረዓለም ደምሴ ከብሎክ እስከ ማዕከል በሚደረገው የንቅናቄ መድረክ ላይ 513500 ወጣቶች እንደሚሳተፉ አሳውቀዋል፡፡ የንቅቄ መድረኩ ከወጣት አደረጃጀቶች እና ነጻ ወጣቶች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ያመላከቱት አቶ ክብረዓለም ወጣቶች የከተማችንን ሰላም ለማጽናትና በማስፈን ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.