
የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ያስችላል
አቶ በላይ ደጀን
ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት ባሻገር በትምህርት ማህበረሰቡ መካከል የወድማማችነትን እና የእህትማማችነትን ግንኙነት እንደሚያጠናክር አስታወቁ
የትምህርት ቤቶች ስፓርታዊ ውድድር ለሰላም ለአብሮነት እና ለሁለተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል ትላንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድምቀት የተከፈተው የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስፓርታዊ ውድድር በፍጹም ስፓርታዊ ጨዋነት እንዲጠናቀቅ ቢሮ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል
የነገ ሃገር ተረካቢ የሆኑ ተማሪዎች በአካል፣በአዕምሮ እና በሥነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ ስፖርት ወሳኝ ነው ያሉት አቶ በላይ በኢትዮጵያ ስፓርት ዘርፍ አንቱታን ያገኙ ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ አድርገው ያወለበለቡ ብርቅዬ ስፓርተኞች መነሻ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን አውስተዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.