በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት መዋቅራዊ አደ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ውይይት ተካሄደ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት መዋቅራዊ አደረጃጀት ጥናት ውይይት ተካሄደ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት መዋቅራዊ አደረጃጀት ሰነድ ጥናት ዙሪያ ከክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች እና ከስራ አስኪያጆች ጋር ውይይት አካሄደ የማዕከላትን በሰው ኃይል ለማደራጀት በትኩረት እየተሰራ ያለውን ስራ ጥናቱ ምላሽ እንደሚሰጥ የገለጹት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር ዓለም ደምሴ ከአመራሩ እና ከባለሙያው የሚነሱ ጥያቄዎች ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል መዋቅር በአንድ ጀንበር የሚለወጥ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ በየጊዜው በሚደረግ ጥናትና ምርምር ሊሻሻል እንደሚችል ያመላከቱት አቶ ክብር ተቋም ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ራስን የመለወጥ እና ሞያዎች የማሻሻል ስራ አብሮ መከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል። የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ሁሉንም አገልግሎት ለማሳደግ የቢፒአር ጥናቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለጹት የወጣቶች ማብቃት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ንብረት ይሁኔ በጀት ዓመቱን ውጤታማ ሆኖ ለመፈጸም ከሰንዱ ባሻገር በራስ አቅም የሚሰሩ ስራዎች የልማት እና ቅጥር ጊቢን የማስዋብ ስራ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል በጥናቱ ላይ ገለጻ ያደረጉት የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ልማት ቡድን መሪ አቶ ሳሙኤል ምትኩ ሰነዱ ባካተታቸው መደቦች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገልጻ አድርገዋል

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.