የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ከትምህርት ቢሮ ጋር ልምድ ልውውጥ አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ከትምህርት ቢሮ ጋር ልምድ ልውውጥ አካሄደ። ታህሳስ 15 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ልምድ ልውውጥ አካሄደ። ልምድ ልውውጡ በዋናነት በአጠቃላይ የቢሮው አደረጃጀት ፣ በሪፎርምና መልካም አስተዳደር ስራዎች፣ በእቅድና ቅንጅታዊ አሰራር እንዲሁም በኮሙኒኮሽን አግባቦች ላይ ያተኮሩ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖሮት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ለተከታታይ አመታት ውጤታማ የሆነ እና ትውልድ ላይ የሚሰራ ተቋም በመሆኑ ልምድ መውሰድ እንደተቻለ ተናግረዋል። በልምድ ልውውጡ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመውሰድ እና ወደ ቢሮው ነባራዊ ሁኔታ በመቀየር በፍጥነት ወደ ስራ እንደሚገባም አቶ በላይ ተናግረዋል። ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ሁለቱ ተቋማት የተለያዩ ስራዎችን በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት ስትራቴጂካዊ አመራር ወሳኝ ነው ብለዋል። የአሰራር ስርዓት መዘርጋትና በእቅድ መመራትን ለውጤታማት ወሳኝ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ይልን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ዳ/ር ዘላለም አስገንዝበዋል። በልምድ ልውውጥ በተዘጋጀ ቸክ ሊስት ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ግልፅነት በሚፈልጉ ጉዳዮችም ምላሽ ተሰጥቷል። ልምድ ልውውጡ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና የጠቅላላ ካውንስል አባላት ተሳትፈወበታል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.