አዲስ አቅም አዲስ ዕድል ለወጣቶች በሚል መሪ ቃ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

አዲስ አቅም አዲስ ዕድል ለወጣቶች በሚል መሪ ቃል የልቦና ውቅር ስልጠና ተሰጠ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም

አዲስ አቅም አዲስ ዕድል ለወጣቶች በሚል መሪ ቃል የልቦና ውቅር ስልጠና ተሰጠ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከልደታ ክፍለ ከተማ እና ከዓለም አቀፉ ወጣቶች ፊሎሺፕ ጋር በመተባበር አዲስ አቅም አዲስ ዕድል ለወጣቶች በሚል መሪ ቃል የልቦና ውቅር /ማይንድ ሴት/ስልጠና ተሰጠ ወጣቶችን በምግባር ለማነጽና የስራ ባህልን ለማዳበር ተሞክሮን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብር-ዓለም ደምሴ የነገ ሃገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ወጣትነት ዕድሜ እጅ ላይ እንዳለ እንቁላል በአግባቡ ይዘን ከጠቀምንበት ለነገ የሚሆን ጥሪት መያዝ ያስችለናል ያሉት የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ ከስልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀት ሕይወታቸውን ለመለወጥ እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ በበኩላቸው ወጣቶች ባገኙት ስልጠና ራሳቸውን እና አገር ለመለወጥ እንዲሰሩ አሳስበው እንዲህ አይነት ስልጠናዎች በወጣቶች ዘንድ የአመለካከት ለዉጥ ለማምጣት በጎ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። በማይንድ ሴት ጠቀሜታ፣ ለወጣቶች ስለሚስገኘው ዕድል ሰፊ ገለጻ ያደረጉት የIYM ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ናም ወጣቶች በበጎ ሐሳብ ከተሞሉ ራሳቸውን አገርን መለወጥ እንደሚችሉ አስገንዝበዋል፡፡

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.