የሀገራችን መፃኢ እድልና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የሀገራችን መፃኢ እድልና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን በእጅጉ ለማስፋት ምክንያታዊ ወጣት ሊፈጠር ይገባል" አቶ ዳዊት ትርፉ

የሀገራችን መፃኢ እድልና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን በእጅጉ ለማስፋት ምክንያታዊ ወጣት ሊፈጠር ይገባል" አቶ ዳዊት ትርፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለክፍለ ከተማው ነዋሪ ሴቶችና ወጣቶች የማይንድ ሴት ስልጠና ሰጥቷል ። በስልጠና መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ እንደገለፁት ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ህዝቦች ቁጥር ባለቤት ናት ያሉ ሲሆን ከዚህም ውስጥ አብዛኛውን ፐርሰንት የሚሸፍነው ወጣቱ በመሆኑ የሀገራችን መፃኢ እድልና አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን በእጅጉ ለማስፋት ምክንያታዊ ወጣት ሊፈጠርና ደካማ የስራ ባህልን በመቅረፍ ሰርቶ መለወጥ ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል ። በለውጡ ዓመታት በርካታ የኢኮኖሚ መገጫዎች የተሰሩ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ዳዊት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የዚህ ትውልድ መገለጫ አሻራ መሆኑን ጠቅሰው ወጣቱ የለውጡ አካል በመሆንና አለም የደረሰበት የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ለመድረስ የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት የተገኙ እድሎችን በመጠቀም መስራትና መለወጥ እንዳለበት አሳስበዋል ። የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም በቀለ በበኩላቸው ስልጠናው የተዘጋጀው በስራ ፈላጊነት ለተመዘገቡና በቀጣይ ስራ ለሚፈጠርላቸው ሴቶችና ወጣቶች በመሆኑ የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ስልጠናውን በትኩረት መከታተልና ወደ ራስ ወስዶ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል ። የማንይድ ሴት ስልጠናው በአሰልጣኝ አቶ ዘላለም ይትባረክ አማካኝነት ሰፊ ግንዛቤ የተፈጠረ ሲሆን ወጣቱ ስራ ለመስራት በቅድሚያ ራሱን ዝግጁ ማድረግና ስንፍናን በማስወገድ ለማንኛውም ስራ ቁርጠኛ መሆንና በላቡ መቀየር ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል ። በአስተሳሰቡ የተገነባ አካባቢውን እና አገሩን መቀየር የሚችል ወጣት በማፍራትና ድህነትን ለማሽነፍ በሚደረገው ብርቱ ርብርብ ወጣቱን አጋዥ ለማድረግ የማይንድ ሴት ስልጠናው ወሳኝ በመሆኑ ሴቶችና ወጣቶች በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያላቸውን አመለካከት እና አስተሳሰብ የመለወጥ ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ በአግባቡ መተግበር እንዳለባቸው ተገልጿል ። በስልጠናው ከ12ቱም ወረዳ የተውጣጡ የስራ ዕድል የሚፈጠርላቸው ሴቶችና ወጣቶች ተሳትፈዋል ። የካ ኮሙኒኬሽን

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.