የኮሪደር ልማቱ እየተመራ ያለው ማስተካከልን፣ ማዘመንን፣ማሳመርንና ማመቻቸትን ገዥ መርሕ በማድረግ ነው!
የኮሪደር ልማቱ እየተመራ ያለው ማስተካከልን፣ ማዘመንን፣ማሳመርንና ማመቻቸትን ገዥ መርሕ በማድረግ ነው! አዲስ አበባን ህይወት አልባ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ መንገድ እና በመንገድ ዙሪያ ያሉ ችግሮች ናቸው፡፡ አገናኝ መንገድ ባለመኖሩ አቃቂና ቃሊቲ እንደ አይንና ቅንድብ የቅርብ ሩቅ ሆነው ሳይተያዩ ቆይተዋል፡፡ መንገድ የሌለው ከተማ እንኳን ሥሉጥ ከተማ ለመሆን የከተማ ደረጃን በቅጡ ለማሟላት አይቻልም፡፡ እነዚህን መሰረታዊ መዋቅራዊ የአዲስ አበባ ችግሮች በመፍታት የቀጣይ ዘመን ከተማ እንድትሆን የኮሪደር ልማትን ተግባራዊ ማድረግ በጥሩ እመርታ ላይ ይገኛል፡፡ ለአዲሰ አበባ የኮሪደር ልማት ቢያንስ ሰባት ጥቅሞችን አስገኝቶላታል፡፡ የመኪና መንገድ ማሻሻያ፣ አረንጓዴ ስፍራዎች፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች ፣ የነዋሪዎች መገልገያ ሥፍራዎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች ግንባታ፣ የንግድ አካባቢዎች ማሻሻያና የመኖሪያ መንደሮች ማሻሻያ፡፡ በአጠቃላይ የኮሪደር ልማቱ እየተመራ ያለው ማስተካከልን ፣ ማዘመንን፣ማሳመርንና ማመቻቸትን ገዥ መርሕ በማድረግ ነው ፡፡ የመደመር መንግሥት ገጽ (242፣2018 ዓ.ም)
እንዲህ ያለ ቃሉን መፈፀም፣ ወደ ተግባር መለወጥ የማይታክት የተደመረ ዓቅም ስላለ በአጭር ጊዜ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ ማድረግ ተችሏል፡፡ ወደፊትም በላቀ የአመራር ብቃት፣ የህዝብ ቅንጅት እና ፍጥነት የታከለበት ፈጠራ ተግባራዊ በማድረግ፣ ከተማችን ብሎም ሃገራችን ወደ የላቀ የብልፅግና ማማ የማድረስ ህልማችንን እውን እናደርጋለን፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.