አሳባሳቢ ገዢ ትርክት ለሀገር መንግስት ግንባታ በሚል መሪ ቃል የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።
አሳባሳቢ ገዢ ትርክት ለሀገር መንግስት ግንባታ በሚል መሪ ቃል የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።
ታህሳስ 18 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አሳባሳቢ ገዢ ትርክት ለሀገረ መንግስት ግንባታ በሚል መሪ ቃል የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማስጀመሪያ ፕሮግራም በጉለሌ ክፍለ ከተማ አካሄደ።
በአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የሚለያዩ ነጠላ ትርክቶችን በማስወገድ አብሮነትን የሚያጠናክሩ አሰባሳቢ ገዢ ትርክቶችን በማሰረፅ እንደሚገባ ተናግረዋል።
አባቶቻችን በደምና እና በህይወት መሰዋት ነፃነቶን አስጠብቀው ያስረከቡንን ሀገር እኛ የዚህ ዘመን ትውልዶች የላብ ዋጋ በመክፈል የበለፀገችና የነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ሀገርን ለመጭው ትውልድ የማስረከብ እዳ አለብን ሱሉ አቶ ዳዊት ገልፀዋል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህል በማድረግ አብሮነትን፣ ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትን እና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ ተናገረዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ቅርጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ይከበር ስማቸው ስፖርት የኢትዮጵያን ስምና ሰንደቅ አለማን በአለም ላይ ከፍ ብሎ እንዲሰማና እንዲውለበለብ በማድረግ የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚያሳይና የሚያስተዋውቅ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም አካል ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የወጣቶችን ስብዕና ለመገንባት እና ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት በጉለሌ ክፍለ እና በመዲናዋ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን አቶ ይከበር ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በልጆቻ ታፍራና ተከብራ የኖረች የነፃነት ቀንድል ናት ያሉት አቶ ይከበር ወጣቱ ትውልድ ይህን በማስቀጠል ብልፅግናናን በማረጋገጥ ለቀጣይ ትውልድ ሊያስተላልፍ ይገባል ሲሉ አቶ ይከበር ተናግረዋል።
ዛሬ በተካሄደው የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀ ግብር ላይ የከተማ የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦችና ነዋሪዎች በስፋት የተሳተፉበት ሲሆን ሁለተኛውን የብዙሀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ልደታ ክፍለ ከተማ እንዲያዘጋጅ ተመርጧል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.