16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል ተጀመረ። ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም

16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል ተጀመረ። ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ 16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል ''የባህል ስፖርቶች ተደራሽነት ለሀገር ማንሰራራት'' በሚል መሪ ቃል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተናጋጅነት መካሄድ ጀመሯል። በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መገለጫ የሆኑት የባህል ስፖርቶች አብሮነትን፣ ወንድማማችነን እና እህትማማችነትን ለማጠናከርና ህብረብሔራዊ አንድነትን ለማጎልበት ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ከትውልድ ወደ ትውልድ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። የባህል ስፖርቶች ለዘመናዊ ስፖርት መነሻ ናቸው ያሉት አቶ በላይ በከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ቤቶች የታዳጊዎች ወጣቶች የባህል ስፖርት የስልጠና ፕሮጀክቶች በመክፈት ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የውድድሩ ዋና አላማም ከተማ አስተዳደሩን ወክለው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር የሚሳተፉ ውጤታማ ስፖርተኞችን መምረጥ እንደሆነ የቢሮ ሀላፊው አሳውቀዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ የባህል ስፖርቶች ጨምሮ በሌሎች የስፖርት አይነቶች ክፍለ ከተማውን ብሎም ከተማውን የሚወክሉ ውጤታማ ስፖርተኞችን ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ልመት እና ለታዳጊ ወጣቶች ስልጠና በክፍለ ከተማው ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን አቶ አድማሱ አሳውቀዋል። የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ወ/ሮ ሂወት መሀመድ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለባህል ስፖርቶች ልዩ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ኢትዮጵያዊ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌሰቲቫል እንድታዘጋጅ መመረጧን ገልፀዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በሀረሪ ክልል ለሚካሄደው 23ኛው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ለ19ኛው የባህል ፌስታቫል ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የቅድመ ዝግጅት ውድድር ማካሄድ መጀመራቸውን ወ/ሮ ሂወት ተናግረዋል። https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.