የኤሊት ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የአቋም መለኪያ ው...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የኤሊት ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የአቋም መለኪያ ውድድር ፌስቲቫል በአራት ኪሎ ፕላዛ ተካሄደ

የኤሊት ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የአቋም መለኪያ ውድድር ፌስቲቫል በአራት ኪሎ ፕላዛ ተካሄደ

ዋን ላቭ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የውድድሩ ሻምፒዮና ሆኗል።

ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ

በአራት ኪሎ ፕላዛ የተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሊት ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌድሬሽን ያዘጋጀው የክለቦች የአቋም መለኪያ ውድድርና ፌስቲቫል በዋን ላቭ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ክለብ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

የአቋም መለኪያ ውድድር መካሄዱ ክለቦችና ስፖርተኞች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ያስችላል ያሉት የስፖርት ማህበራት ውድድር ማደራጃ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌው ታደለ ውድድሩ በኮሪደር ልማት በደመቁ አደባባዮች መካሄዱ ለነዋሪው ተጨማሪ መዝናኛ እንደሚሆኑ ገልጸዋል

ለተተኪ ስፖርተኞች የውድድር ልምድ እንዲያገኙ እድል የሚፈጥር ውድድሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለጹት የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ደረስ ለውድድሩ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል

በወንዶች እና በሴቶች በፓተርንና በፋይት፣ በተጠና ስፕሪንግ ዋን ላቭ ኢንተርናሽናል ክለብ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል

በወንዶች በፓተርንና በፋይት፣ በተጠና ስፕሪንግ ኑር ታለንት ኢንተርናሽናል ክለብ ሲያሸንፍ በሴቶች በፓተርንና በፋይት ዋን ላቭ ኢንተርናሽናል ክለብ ሻምፒዮና መሆኑን አረጋግጧል

በ2018 የአቋም መለኪያ ሻምፒዮና ውድድር ለተሳተፉ ዳኞች በውድድሩ ለተሳተፉ ክለቦችም የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በውድድሩ ቢ.ኤች፣ ዋን ላቭ፣ዜድ ላዮን ሮሕቦት፣ኒው ታርጌት፣ዘ ሰን፣አስራት፣ ጋሻ እና ኑር ታለነት ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ክለቦች ተሳታፊ መሆናቸው ተመልክቷል

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.