ኮሪደር ልማቱ የመዲናዋን መልካም ገፅታ ከመገንባት ባሻገር ተተኪ ስፖርተኞች በብዛትና በጥራት እንዲፈሩ እድል የፈጠረ ነው። አቶ በላይ ደጀን
ኮሪደር ልማቱ የመዲናዋን መልካም ገፅታ ከመገንባት ባሻገር ተተኪ ስፖርተኞች በብዛትና በጥራት እንዲፈሩ እድል የፈጠረ ነው። አቶ በላይ ደጀን ታህሳስ 19 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የብስክሌት ፌዴሬሽን አመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና የፍፃሜ ውድድሩን ከተባበሩት አደባባይ ወደ ፍየል ቤት በኮሪደር ልማት በተገነባው መንገድ ላይ አካሂዷል። በውድድሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የኮሪደር ልማቱ የመዲናዋን መልካም ገፅታ ከመገንባት በተጨማሪ የብስክሌት ስፖርትን ጨምሮ በየስፖርት አይነቱ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት እንዲፈሩ እድል የፈጠረ ነው ብለዋል። ከተወሰነ አመት በፊት በመዲናዋ ጥቂት የሚባሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ቢኖሩም ከእግር ኳስ ሜዳ የዘለለ ሌሎች የስፖርት አይነቶችን ያካተቱ እንዳልነበሩ አቶ በላይ አስታውሰው ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በመዲናዋ የተገነቡ ከ1530 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በከተማዋ ያሉ 38 የስፖርት ፌዴሬሽኖችን እና አሶሴሽኖችን ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ብለዋል። ለአራት ተከታታይ ሳምታት በተለያዩ የኮሪደር ልቶች ሲካሄድ የቆየውና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኝው አመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ዋና አላማም የኮሪደር ልማቶችን ለህብረሰቡ የማስተዋወቅና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የብስክሌት የታዳጊዎች ምዘና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የሚወክሉ ውጤታማ ስፖርተኞችን ለመምረጥ እንዲሁም የክለቦችን አቋም ለመለካት እንደሆነ አቶ በላይ ገልፀዋል። በውድድሩ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የጤና ቡድኖች እና ክለቦች የተሳተፉበት ሲሆን ለአሸናፊዎች የሜዳልና የዋንጫ የገንዘብ ሽልማት ከአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ተበርክቶላቸዋል። https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.