
ፌድሬሽኑ የክለቦች የክብደት ማንሳት ሻምፒዮና ውድድር በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የሶፊ ማልት የተማሪዎች የሩጫ ውድድርን ቦሌ መድኃኒያለም ትምህርት ቤት ሻምፒዮና ሆኗል
ግንቦት 12 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ክብደት ማንሳትና ሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የ2016 የክለቦች ክብደት ማንሳት ሻምፒዮና ውድድር በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለቦ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
በጃን ሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሲካሄድ በቆየው የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ከየካታጎሪው አሸናፊ ለሆኑ ክለቦች የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል
ውድድሩ ክለቦች አቋማቸውን ለመለካት ከማስቻሉ ባሻገር የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የሚሳተፉ ክለቦችን ለመለየት ያስችላል ያሉት የፌድሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን አበበ በቀጣይ ሳምንት የቅርጽ ውድድር እንደሚካሄድ ጠቁመዋል
በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከሶፊ ማልት ጋር በመተባበር ሲካሄድ በቆየው የ2016 ሶፊ የተማሪዎች ውድድርን ቦሌ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት በበላይነት በማጠናቀቅ የ50ሺ ብር ተሸላሚ ሆነ
ውድድሩን በአንደኛነት ያጠናቀቀው ቦሌ ማህበረሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ50ሺ ብር ተሻላሚ ሲሆን ውድድራቸው 2ኛ እና 3ኛ ሆነው ያጠናቀቁት ዳግማዊ ምንሊክ እና ወይዘሮ ቀለምወርቅ ትምህርት ቤት የ30ሺ እና የ25ሺ ብር ተሸላሚ ሆነዋል
ፌድሬሽኑ ከሶፊ ማልት ጋር በመተባበር ለሳምንት ሲያሰለጥናቸው የቆዩ 300 ተማሪዎች የተሳተፉበት ውድድር ላይ ትምህርት ቤቶች በ100ሜ በ200ሜ በ400ሜ በ800ሜ እና በ1500ሜ በሁለቱም ጾታ ከፍተኛ ፉክክር ማድረጋቸው ታውቋል
በሶፊ ማልት 2016 የተማሪዎች ውድድር በየካታጎሪው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ሆነው ያጠናቀቁ አትሌቶች የሜዳልያ፣የገንዘብ እና የቁሳቁስ ሽልማት ከእለት የክብር እንግዶች ተበርክቶላቸዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.