የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቆሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ገመገመ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቆሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ገመገመ። ታህሳስ 21ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቆሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ገመገመ። ቋሚ ኮሚቴው ቢሮው ወጣቶች በከተማቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን በቅንጅት እየሰራቸው ያሉ ስራዎች ውጤታማ በመሆናቸው በቀጣይ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አመላክቷል። የከተማውን ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቢሮው ለስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማት፣ ለታዳጊ ወጣቶች ስልጠና፣ ለማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲሁም ለስፖርታዊ ውድድሮች እና ፌስቲቫሎች የሰጠውን ልዩ ትኩረት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በምልከታ እና በሪፖርት ማረጋገጥ እንደቻሉ ተናግረዋል። በቀጣይ ቢሮው በወጣቶች ሁለንተናዊ ስብዕና ግንባታ፣ የስራ እድል ፈጠራ እና ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ከማፍራት አኳያ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባው ቋሚ ኮሚቴው አሳስቦል። በቋሚ ኮሚቴው ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በቀጣይ በቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ ለከተማው ወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ለከተማዋ የስፖርት እድገት ቢሮው በትኩረት አንደሚሰራ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን የቢሮው የእቅድና በጀት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አበባየሁ ለቋሚ ኮሚቴው በዝርዝር አቅርበዋል። https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.