በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲስ አቅም አዲስ ዕድል ለወጣቶች በሚል መሪ ቃል ለወጣቶች የማይንድ ሴት ስልጠና ተሰጠ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲስ አቅም አዲስ ዕድል ለወጣቶች በሚል መሪ ቃል ለወጣቶች የማይንድ ሴት ስልጠና ተሰጠ። ታህሳስ 22 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር አዲስ አቅም አዲስ ዕድል ለወጣቶች በሚል መሪ ቃል የማይንድ ሴት ስልጠና ተሰጥቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብራለም ደምሴ ስልጠናው የነገ ሃገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚስችል አስተሳሰብ እንዲይዙ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል። ስልጠናው የወጣቶችን የስራ ባህል በማዳበርና የወጣትነት አቅማቸውን በመጠቀም ውጤታማ ተግባራትን መስራት እንዲችሉ ያበረረታል ያሉት አቶ ክብራለም ወጣት በተሰጠው እድል ተጠቅሞ ሀገርን ለመገንባት የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት የሚጠይቅ መሆኑንም ገልጸዋል። የቢሮው የወጣቶች ስብእና ልማት ቡድን መረ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ምትኩ ወጣትነት ሙሉ አቅምን፣እውቀትንና ክህሎትን ተጠቅሞ ለመጪው ጊዜ መሰረት የሚሆን የህይወት መስመር የሚዘረጋበት አልባሌና አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ንቆ በመተው ጊዜን ሙሉ በሙሉ ለጠቃሚ ነገሮች በማዋል ተዓምር የሚመስሉ ነገሮችን ማሳካት የሚቻልበት የእድሜ ክልል መሆኑን በማውሳት በዚህ ስልጠና የተሳተፉ አካላት በስልጠና ያገኙትን እውቀት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በህይዎታቸው ተጨባጭ ለውጥና ስኬት ለማምጣት መትጋት እንደሚኖርባቸውም ተናግረዋል። ገለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.