በከተማ አስዳደሩ የተዋቀረ ሱፐርቪዥን ቡድን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ላይ ምልከታ አካሄደ።
በከተማ አስዳደሩ የተዋቀረ ሱፐርቪዥን ቡድን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ላይ ምልከታ አካሄደ። ታህሳስ 22 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀምን የሰነድና የአካል ምልከታ አካሄደ። የሱፐርቪዥን ቡድኑ በ6ወራት ውስጥ የተሰሩ የእቅድ ዝግጅት ስራዎች፣ የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ስራዎች፣ የኢንሼቲቭ ተግባራት፣ የወጣቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲሁም በከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት ልማት ስራዎች በተመለከተ የተግባራት አፈፃፀም ላይ ትኩረት አድርጎ ምልከታ አካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አሰሰተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የቢሮውን 6ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከቅድመ ዝግጅት ስራዎች እስከ ዋና ተግባራት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የከተማውን ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም በስፖርት ልማት እድገትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል። ቢሮው በ6 ወራት ውስጥ ከመደበኛ ስራዎች በተጨማሪ በበጎ ፍቃድና በኢንሸቲቭ ተግባራት የሰራቸው ስራዎች የሰነድና የአካል ምልከታ በማድረግ ውጤታማ ስራ መሰራቱን የሱፐርቪዥን ቡድኑ ማረጋገጡን የገለፀ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት ተደርጎባቸው ሊሰሩ የሚገባቸውን ስራዎች አመላክቷል። https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.