ቢሮው በከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ዙሪ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ቢሮው በከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ዙሪያ ከአንጋፋ ስፖርተኞችና ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ። ታህሳስ 23 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ቢሮው በከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ዙሪያ ከአንጋፋ ስፖርተኞችና ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ። ታህሳስ 23 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ዙሪያ ከአንጋፋ ስፖርተኞችና ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተሳታፊዎች ጋር በ4ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀንን ጨምሮ በአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ለረጅም አመት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሰሩ እና በተለያዩ የስፖርት አይነት ለክለብ እና ለብሔራዊ ቡድን ተጫውተው ያሳለፉ አንጋፋ ስፖርተኞች ተሳትፈውበታል። ከተማ አስተዳደሩ ለስፖርቱ በሰጠው ልዩ ትኩረት ማህብረሰቡ በሚኖርበት፣ በሚሰራበት እና በሚማርበት አከባቢ የስፖርት መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት ተተኪ ስፖርተኞች የሚፈሩበት እና ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አቶ በላይ ደጀን ተናግረዋል። ስፖርት እድሜ፣ ፃታ፣ ዘር፣ ሀይማኖት፣ቋንቋ እና ፖለቲካ የማይገድበው ሁሉንም በአንድ መድረክ የሚያገናኝ እና ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር የእርስ በእርስ ግንኙነትን በመፍጠር አብሮነትን፣ አንድነትን፣ ወድማማችነትን እና እህትማማችነትን የሚያጠናክር መሆኑን አቶ በላይ ተናግረዋል። የ4ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠናን ማዕከልን ጨምሮ ለህብረተሰቡ ጤናውን የሚጠብቅባቸው በከተማው የሚገኙ ሌሎች የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላትን የሚሰጡትን አገልግሎት የማሻሻል፣ የማዘመን እና ቁጥራቸውንም ለመጨመር በትኩረተ እንደሚሰራ የቢሮ ሀላፊው አሳውቀዋል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አንጋፋ ስፖርተኞችም በከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ትውልድን መሰረት ያደረጉ እና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው መደሰታቸውን ተናገረዋል። በቀጣይ ባላቸቸው እውቀትና ሰፊ ልምድ ለከተማዋ ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚወጡ የተናገሩ አጋፋ ስፖርተኞች በከተማው የሚገኙ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት እንዲስፋፉ እና በግብዓት እንዲሞሉ ጠይቀዋል። https://linktr.ee/YouthandSport1

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.