ፌድሬሽኑ ያዘጋጀው የስፓርት ፌስቲቫል በቲናው M...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ፌድሬሽኑ ያዘጋጀው የስፓርት ፌስቲቫል በቲናው MD ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ አሸናፊነት ተጠናቀ

ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌድሬሽን ጋር በመተባበር ጽዱ ኢትዮጵያ ለአዲስ አበባ በሚል መሪ ቃል የተካሄደው የቴኳንዶ ስፖርት ፌስቲቫል በቲናው በMD ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ቲናው MD ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ክለብ የፌስቲቫሉ ሻምፒዮና ሲሆን NKF እና MD. MR ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ክለቦች 2ኛ እና 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል

ፌስቲቫሉን መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ቸሩ ኩሳ እንዲህ አይነት ፌስቲቫሎች የእርስ በእርስ ግኑኝነትን ከማጠናከራቸው ባሻገር ክለቦች ለሚያደርጉት ውድድር እና ስልጠና በር ከፋች ነው ብለዋል

በፌስቲቫሉ ላይ 28 ያክል ክለቦች በሁለቱም ፆታ ከህፃናት እስከ አዋቂ ከቢጫ በአረንጓዴ እስከ 5ኛ ዳን የቀበቶ ደረጃ ያላቸዉ ከ350 በላይ ሰፖርተኞች መሳተፋቸውን የገለጹት የፌድሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ የውብዳር ከተማ ውድድሩን ለመሩ ዳኞችና ተሳታፊ ክለቦች ለክለብ አስልጣኞች :ለአሰልጣኝ ማህበር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና አስተዋፅዖ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል

በፌስቲቫሉ ላይ ነጠላ ፓተርን የቡድን ፓተርን ቅድመ ዝግጁ ነፃ ፍልሚያ ሞዴል ነፃ ፍልሚያልዩ ቴክኒክ ሰበራ አይነቶችን ያካተተ ትሪኢታቸውን ክለቦች አቅርበዋል ::

ፌስቲቫሉ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ሆነው ያጠናቀቁ ክለቦች የተዘጋጀላቸውን የዋንጫ ሽልማት እና ማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.