በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በከተማ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በከተማ አቀፍ ደረጃ 20 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ / ከንቲባ አዳነች አቤቤ / ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በከተማ አቀፍ ደረጃ 20 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ / ከንቲባ አዳነች አቤቤ /

ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በከተማ አቀፍ ደረጃ 20 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

በመዲናዋ “የምትተክል ሀገር- የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ከንቲዋን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተጀምሯል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተጀመረው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች ባደረጉት ንግግር፣ “ከተማችንን አረንጓዴ የምናደርጋት እኛው ነን፤ ይህንን የምናደርገው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ጭምር ነው" ብለዋል።

የምንተክለው ችግኝ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ መተባበርን እና አብሮ መኖርን ጭምር ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አዲስ አበባ በየዓመቱ የምትተክላቸውን ችግኞች ቁጥር እያሳደገች መምጣቷን የጠቀሱት ከንቲባዋ፣ ባለፈው ዓመት 17.5 ሚሊዮን ተክለናል፤ ዘንድሮ 20 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እንሠራለን ብለዋል።

ዛሬ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሩ ክረምቱን ሙሉ የሚዘልቅ መሆኑን ገልጸው፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ባለሃብቶች፣ ዲፕሎማቶች እና ሁሉም አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ አደራ ብለዋል።

"የምንተክለው የጥላ ዛፍ፣ ምግባችንን፣ የአየር ፀባይ ለውጥ መከላከልን፣ ጤናችንን ጭምር ነውና ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን የተከልነውን እንደ ልጆቻችን በመንከባከብ ውጤታማ ልናደርጋቸው ይገባል" ሲሉም አሳስበዋል።

የመረጃ ምንጭ የአዲስ ሚዲያ ኔትወር/AMN/ ነው

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

80Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 78 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.