በአምስተኛው አረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በአምስተኛው አረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የስፓርት ቤተሰቦችና አንጋፋ አትሌቶች መሳተፋቸው ተገለጸ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በአምስተኛው አረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የስፓርት ቤተሰቦችና አንጋፋ አትሌቶች መሳተፋቸው ተገለጸ

ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሲያስጀምሩ አንጋፋ አትሌቶች የስፓርት ቤተሰቦች እና ወጣቶች መሳተፋቸው ተገለጸ

የምንተክለው ችግኝ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ መተባበርን እና አብሮ መኖርን ጭምር ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ ባለፈው ዓመት 17.5 ሚሊዮን ችግኝ መትከልዋን አስታውሰው ዘንድሮ 20 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ ይፋ አድርገዋል

"የምንተክለው የጥላ ዛፍ፣ ምግባችንን፣ የአየር ፀባይ ለውጥ መከላከልን፣ ጤናችንን ጭምር ነውና ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን የተከልነውን እንደ ልጆቻችን በመንከባከብ አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች በመርህ ግብሩ ላይ የተገኙ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ባለሃብቶች፣ ዲፕሎማቶች እና ሁሉም አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የዘንድሮ የአምስተኛውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በስኬት ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸው ባለፉት አምስት ዓምታት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እንዲሳካ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች የተጫወቱትን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል

አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጭነት በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራር ሰጪነት በመዲናችን በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ በላይ የከተማችን 70 ከመቶ የሆነው ወጣት እና የስፓርት ቤተሰቦችን በማሳተፍ 1.5 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከል አሳውቀዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

119Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 117 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.