
አዲስ አበበ ከተማ የኦሎምፒክ ችቦን ከድሬደዋ ከተማ ተረከበ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
አዲስ አበበ ከተማ የኦሎምፒክ ችቦን ከድሬደዋ ከተማ ተረከበ
ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
ኢትዮጵያ ትወዳደር ተወዳድራም ታሸንፍ በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያው ችቦ በመቀሌ በይፋ ተለኩሶ በሁሉም ክልሎች ሲዘዋወር የቆየው የመልካም ምኞት ችቦ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማጠቃለያ ዝግጅት ከድሬደዋ ከተማ ተረከበ
በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም በተከናወነው ችቦ የማብራት ስነ-ስርዓት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁአር፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ፣የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የድሬዳዋ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሐመድ፣የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ የድሬደዋ ከተማ ነዎሪዎች እና የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ባስተላለፉት መልዕክት ለኦሎምፒክ ቡድኑ ውጤታማነት ከተማ አስተዳደሩ የሚያስፈልገውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸው ጀግኖች አትሌቶች ያስለመዱንን ድል በማስመዝገብ ሰንደቅ ዓላማችን ከፍ አድርገው ለማውለብለብ ታላቅ አደራ አለባቸው ብለዋል።
በፓሪስ ኦሎምፒክ ውጤታማ ለመሆን ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ የገለጹትየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አትሌቶችን በማበረታት ከጎናቸው እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል
ከድሬደዋ ከተማ የተረከብነው የመልካም ምኞት ችቦ በአዲስ አበባ ከተማ ታላቅ ኮንሰርትን ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች ለአንድ ሳምንት ይቆያል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ኢትዮጵያ በጀግኖች አትሌቶችዋ አመርቂ ውጤት እንደምታስመዘግብ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል
የኦሎምፒክ ችቦ የማብራት የማጠቃለያ ዝግጅትን በማካሄድ በውድድሩ ለሚሳተፍ አትሌቶች መልካም እድል እንዲገጥማቸው በመመኝት እርክክብ እንደሚደረግ የገለጹት አቶ ዳዊት በስነስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ስፖርተኞች ታዋቂ ሰዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ገልጸዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
134You፤ Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 131 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.